በዚያም ወራት በይሁዳ በሰንበት ቀን የወይን መጥመቂያን የሚረግጡትን፥ ነዶም የሚከመሩትን፥ የወይኑን ጠጅና የወይኑን ዘለላ በለሱንም ልዩ ልዩም ዓይነት ሸክም በአህዮች ላይ የሚጭኑትን፥ በሰንበትም ቀን ወደ ኢየሩሳሌም የሚያስገቡትን አየሁ፥ ገበያ ባደረጉበትም ቀን አስመሰከርሁባቸው።
ኤፌሶን 4:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ አሕዛብ በአእምሮአቸው ከንቱነት እንደሚመላለሱ ከእንግዲህ ወዲህ እንዳትመላለሱ እላለሁ፥ በጌታም እለምናችኋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ይህን እነግራችኋለሁ፤ በጌታም ዐደራ እላለሁ፤ በአስተሳሰባቸው ከንቱነት እንደሚኖሩት እንደ አሕዛብ ልትመላለሱ አይገባም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእንግዲህ ወዲህ ሐሳባቸው ከንቱ እንደሆነው እንደ አሕዛብ አትኑሩ ብዬ በጌታ ስም አስጠነቅቃችኋለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ በልባቸው ከንቱ አሳብ እንደሚኖሩ እንደ አሕዛብ እንዳትኖሩ ይህን እላለሁ፤ በእግዚአብሔርም እመሰክራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ አሕዛብ ደግሞ በአእምሮአቸው ከንቱነት እንደሚመላለሱ ከእንግዲህ ወዲህ እንዳትመላለሱ እላለሁ በጌታም ሆኜ እመሰክራለሁ። |
በዚያም ወራት በይሁዳ በሰንበት ቀን የወይን መጥመቂያን የሚረግጡትን፥ ነዶም የሚከመሩትን፥ የወይኑን ጠጅና የወይኑን ዘለላ በለሱንም ልዩ ልዩም ዓይነት ሸክም በአህዮች ላይ የሚጭኑትን፥ በሰንበትም ቀን ወደ ኢየሩሳሌም የሚያስገቡትን አየሁ፥ ገበያ ባደረጉበትም ቀን አስመሰከርሁባቸው።
እንዲህም አሉ “እናንተ ሰዎች! ይህን ስለምን ታደርጋላችሁ? እኛ ደግሞ እንደ እናንተ የምንሰማ ሰዎች ነን፤ ከዚህም ከንቱ ነገር ሰማይንና ምድርን ባሕርንም በእርነርሱም ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ትመለሱ ዘንድ ወንጌልን እንሰብካለን።
ምክንያቱም እግዚአብሔርን እያወቁት እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን አላከበሩትም ወይም አላመሰገኑትም፤ ነገር ግን ምክንያታቸው ዋጋ ቢስ ሆነ፤ የማያስተውለው ልባቸውም ጨለመ።
እኔ የምለው፥ እያንዳንዳችሁ “እኔ የጳውሎስ ነኝ፤” “እኔስ የአጵሎስ ነኝ፤” “እኔ ግን የኬፋ ነኝ፤” “እኔስ የክርስቶስ ነኝ፤” ትላላችሁ።
ይህንም እላለሁ፦ ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የመጣው ሕግ፥ የተስፋውን ቃል ለማስቀረት፥ አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠውን ኪዳን ሊሽር አይችልም።
ራስን ማዋረድና የመላእክትን አምልኮ እየወደደ፥ ባየውም ራእይ ላይ በጽኑ እየተመረኮዘ፥ በሥጋዊም አእምሮ በከንቱ እየታበየ ማንም አይፍረድባችሁ፤
አስቀድመን ደግሞ እንደ ነገርናችሁና እንደ መሰከርንላችሁ፥ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና፥ ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ፤ ወንድሙንም አያታልል።
አንዱን ከሌላው በማበላለጥ ምንም ዓይነት ነገር ሳታደርግ፥ ያለ አድልዎ እነዚህን ትዛዛቶች እንድትጠብቅ በእግዚአብሔርና በጌታ በክርስቶስ ኢየሱስ በተመረጡትም መላእክት ፊት አደራ እልሃለሁ።