መክብብ 8:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የንጉሥ ቃል ኃይለኛ ነውና፥ “ይህንስ ለምን ታደርጋለህ?” ማን ይለዋል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የንጉሥ ቃል የበላይ ስለ ሆነ እርሱን፣ “ምን ታደርጋለህ?” ማን ሊለው ይችላል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሁሉን ነገር ለማድረግ ሥልጣን አለው፤ “ለምን ይህን ሠራህ?” ብሎ የሚጠይቀውስ ማን አለ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሥ እንደ መሆኑ ኀይል አለውና፤ ይህንስ ለምን ታደርጋለህ? ማን ይለዋል? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የንጉሥ ቃል ኃይለኛ ነውና፥ ይህንስ ለምን ታደርጋለህ? ማን ይለዋል? |
በእውነት ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፥ በእኔም ፋንታ በዙፋኔ ላይ ይቀመጣል ብዬ በእስራኤል አምላክ በጌታ እንደ ማልሁልሽ፥ እንዲሁ ዛሬ በእውነት አደርጋለሁ” ብሎ ማለ።
ከዚህም በኋላ ለዮዳሄ ልጅ ለበናያ ሺምዒን እንዲገድል ትእዛዝ አስተላለፈ፤ በናያም ሄዶ ሺምዒን ገደለው፤ በዚህም ዓይነት መንግሥቱ በሰሎሞን እጅ የጸና ሆነ።
ከዚያ በኋላ በወንዝ ማዶ ያለ አካባቢ ገዢ ታትናይ፥ ሽታርቦዝናይና ተባባሪዎቻቸው ንጉሡ ዳርዮስ እንደ ላከው ቃል፥ እንዲሁ ተግተው አደረጉ።
ነገር ግን፥ ሰው ሆይ! ለእግዚአብሔር መልስ የምትሰጥ አንተ ማን ነህ? የተሠራ ነገር የሠራውን “ለምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ?” ይለዋልን?