መክብብ 7:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በነፍስህ ለቁጣ ችኩል አትሁን፥ ቁጣ በአላዋቂ ብብት ያርፋልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሞኞች ቍጣ በዕቅፋቸው ውስጥ ስለ ሆነ፣ በመንፈስህ ለቍጣ አትቸኵል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቊጣ የሰነፎች ቂም በቀል መወጫ ስለ ሆነ የቊጡነት ስሜትህን ተቈጣጠር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመንፈስህ ለቍጣ ችኩል አትሁን፥ ቍጣ በሰነፎች ብብት ያርፋልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነፍስህ ለቍጣ ችኩል አትሁን፥ ቍጣ በሰነፍ ብብት ያርፋልና። |
ከዚያም አቤሴሎም አገልጋዮቹን፥ “አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ መንፈሱ መለወጡን ተጠባበቁ፤ እኔ ‘አምኖንን፥ ምቱት’ በምላችሁ ጊዜ ግደሉት፤ ያዘዝኋችሁ እኔው ስለሆንኩ አትፍሩ፤ ብርቱዎች ሁኑ፥ ጨከን በሉም” ብሎ አዘዛቸው።
የዳዊት ወንድም የሻምዓ ልጅ ዮናዳብ ግን እንዲህ አለ፤ “የተገደሉት የንጉሡ ልጆች በሙሉ እንደ ሆኑ አድርጎ ጌታዬ አያስብ፤ የሞተው አምኖን ብቻ ነው። አምኖን እኅቱን ትዕማርን በግድ ከደፈራት ጊዜ አንሥቶ አቤሴሎም ይህን ጉዳይ ቆርጦ የተነሣበት ነበር።
የይሁዳም ሰዎች ሁሉ፥ ለእስራኤል ሰዎች፥ “ይህን ያደረግነው ንጉሡ የቅርብ ዘመዳችን ስለሆነ ነው፤ ታዲያ ይህ እናንተን የሚያስቆጣ ነገር ነው? እኛ ከንጉሡ ተቀብለን አንዳች በልተናልን? ለራሳችንስ ምን የወሰድነው ነገር አለ?” አሉአቸው።
ፀሐይም በወጣ ጊዜ እግዚአብሔር የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ አዘጋጀ፥ ዮናስ ራሱን እስኪስት ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለነፍሱም ሞትን ለመነና “ከሕይወት ሞት ይሻላል” አለ።