ዳዊትም ቤተሰቡን ለመመረቅ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ የሳኦል ልጅ ሜልኮል ግን ልትቀበለው ወጣችና፥ “ዛሬ የእስራኤል ንጉሥ በመኳንንቱ ገረዶች ፊት እንደ አንድ ተራ ሰው ራቁቱን መታየቱ ክብሩ ሆኖ ነው!” አለችው።
መክብብ 7:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እጅግ ክፉ አትሁን፥ አላዋቂም አትሁን፥ ጊዜህ ሳይደርስ ለምን ትሞታለህ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እጅግ ክፉ አትሁን፤ ሞኝም አትሁን፤ ለምንስ ያለ ቀንህ ትሞታለህ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያለ ጊዜህም በሞት እንዳትቀጭ እጅግ ክፉ ወይም ሞኝ አትሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እጅግ ክፉ አትሁን፥ እልከኛም አትሁን፥ ያለ ጊዜህ እንዳትሞት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እጅግ ክፉ አትሁን፥ እልከኛም አትሁን፥ ጊዜህ ሳይደርስ እንዳትሞት። |
ዳዊትም ቤተሰቡን ለመመረቅ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ የሳኦል ልጅ ሜልኮል ግን ልትቀበለው ወጣችና፥ “ዛሬ የእስራኤል ንጉሥ በመኳንንቱ ገረዶች ፊት እንደ አንድ ተራ ሰው ራቁቱን መታየቱ ክብሩ ሆኖ ነው!” አለችው።
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ ይህን አይተሃልን? በዚህ የሰሩትን ርኩሰት ሊያደርጉ ለይሁዳ ቤት ይህ ቀላል ነገር ነውን? ምድሪቱን በዓመፅ ሞልተዋታል፥ ሊያስቆጡኝም ተመልሰዋል፥ እነሆ ቅርንጫፉን ወደ አፍንጫቸው አቅርበዋል።