መክብብ 6:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፀሐይ በታች ያየሁት ክፉ ነገር አለ፥ እርሱም በሰው ላይ እጅግ የከበደ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከፀሓይ በታች ሌላ ክፉ ነገር አየሁ፤ እርሱም ለሰዎች እጅግ የሚከብድ ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዓለም በሰው ሁሉ ላይ የሚደርስ እጅግ የከፋ ነገር ተመለከትኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፀሐይ በታች ያየሁት ክፉ ነገር አለ፥ እርሱም በሰው ላይ እጅግ የበዛ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፀሐይ በታች ያየሁት ክፉ ነገር አለ፥ እርሱም በሰው ላይ እጅግ የከበደ ነው። |
እግዚአብሔር ለሰው ሀብትን፥ ንብረትንና ክብርን ሰጠው፥ ከወደደውም ነገር ሁሉ ለነፍሱ አልጐደለውም፤ ነገር ግን ሌላ ሰው ይበላዋል እንጂ ከእርሱ ይበላ ዘንድ እግዚአብሔር ሥልጣን አልሰጠውም፤ ይህም ከንቱና ክፉ ደዌ ነው።