La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መክብብ 5:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ብርን የሚወድድ ሰው ብርን አይጠግብም፥ ሀብትንም የሚወድድ ትርፉን አይጠግብም፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከምድሩ የሚገኘው ትርፍ ለሁሉም ነው፤ ንጉሡም ራሱ የሚጠቀመው ከዕርሻ ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የመሬት ምርት መጨመር ሁሉንም ይጠቅማል፤ ንጉሡ ራሱ ከእርሻው ይጠቀማል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የም​ድር ጥቅም ለሁሉ ነው፥ የን​ጉ​ሥም ጥቅም በእ​ርሻ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በጠቅላላው ግን የአገሩ ጥቅም እርሻን የሚወድድ ንጉሥ ቢኖር ነው።

Ver Capítulo



መክብብ 5:9
15 Referencias Cruzadas  

ሰማያት የጌታ ሰማያት ናቸው፥ ምድርን ግን ለሰው ልጆች ሰጣት።


በድሆች እርሻ ላይ ብዙ ሲሳይ አለ፥ ከፍርድ መጉደል የተነሣ ግን ይጠፋል።


ምድሩን የሚያርስ እንጀራ ይጠግባል፥ የማይረቡ ሰዎችን የሚከተል ግን ድህነት ይሞላበታል።


አንድ ሰው ብቻውን ይኖራል፥ ማንም አብሮት የለም፥ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፥ ለድካሙም መጨረሻ የለውም፥ ዐይኖቹም ሳይቀሩ ሀብትን አይጠግቡም። እንግዲህ ለማን እደክማለሁ፥ ሰውነቴንስ መልካሙን ነገር ለምን እነፍጋታለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር ክፉም ጥረት ነው።


ሀብት ሲበዛ የሚበሉት ይበዛሉ፥ ሀብቱን በዓይኑ ብቻ ከማየት በቀር ለባለቤቱ ምን ይጠቅመዋል?


በጠቅላላው ይህ ለአገሩ ይጠቅማል፤ ንጉሥም ከእርሻ ይጠቀማል።


የሰው ድካም ሁሉ ለአፉ ነው፥ ነፍሱ ግን አትጠግብም።