መክብብ 5:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሀብት ሲበዛ የሚበሉት ይበዛሉ፥ ሀብቱን በዓይኑ ብቻ ከማየት በቀር ለባለቤቱ ምን ይጠቅመዋል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገንዘብን የሚወድድ፣ ገንዘብ አይበቃውም፤ ብልጽግናም የሚወድድ፣ በትርፉ አይረካም፤ ይህም ከንቱ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብርን የሚወድ ብር አግኝቶ አይጠግብም፤ ሀብታም ለመሆን የሚፈልግም ሰው ትርፍ አግኝቶ በቃኝ አይልም፤ ይህም ከንቱ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብርን የሚወድድ ሰው ብርን አይጠግብም፤ ብዙ እህልንም የሚወድድ እንዲሁ ነው፤ ይህም ከንቱ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብርን የሚወድድ ሰው ብርን አይጠግብም፥ ባለጠግነትንም የሚወድድ ትርፉን አይጠግብም፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው። |
ዐይኖቼ የፈለጉትን እንዳያዩ አልከለከልኋቸውም፥ ልቤም በድካሜ ሁሉ ደስ ይለው ነበርና ልቤን ከደስታ ሁሉ አላራቅሁትም፥ ከድካሜም ሁሉ ይህ እድል ፈንታዬ ሆነ።
እጄ የሠራቻትን ሥራዬን ሁሉ የደከምሁበትንም ድካሜን ሁሉ ተመለከትሁ፥ እነሆ፥ ሁሉ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነበረ፥ ከፀሐይ በታችም ትርፍ አልነበረም።
እርሱም ደስ ለሚያሰኘው ሰው ጥበብንና እውቀትን ደስታንም ይሰጠዋል፥ ለኃጢአተኛው ግን እግዚአብሔርን ደስ ለሚያሰኘው ሰው ይሰጥ ዘንድ እንዲሰበስብና እንዲያከማች ሥራን ይሰጠዋል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
የሰው ልጆችና የእንስሳ እድል ፈንታ አንድ ነው፥ አንድ ዓይነት መጨረሻ ይገጥማቸዋል፤ አንዱ እንደሚሞት ሌላውም እንዲሁ ይሞታል፥ የሁሉም እስትንፋስ አንድ ነው፥ ሁሉም ከንቱ ነውና ሰው ከእንስሳ ብልጫ የለውም።
ከእርሱ በፊት የተገዙለት ሕዝብ ሁሉ ስፍር ቍጥር አልነበራቸውም፥ በኋላ የሚመጡት ግን በእርሱ ደስ አይላቸውም። ይህም ደግሞ ከንቱ፥ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
ደግሞም የሰውን ድካምና የብልሃት ሥራውን ሁሉ ተመለከትሁ፥ በባልንጀራም ዘንድ ቅንዓት እንደሚያስነሣ አየሁ፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
አንድ ሰው ብቻውን ይኖራል፥ ማንም አብሮት የለም፥ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፥ ለድካሙም መጨረሻ የለውም፥ ዐይኖቹም ሳይቀሩ ሀብትን አይጠግቡም። እንግዲህ ለማን እደክማለሁ፥ ሰውነቴንስ መልካሙን ነገር ለምን እነፍጋታለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር ክፉም ጥረት ነው።
“ሁለት ጌቶችን ማገልገል የሚችል ማንም የለም፤ አንዱን ጠልቶ ሌላውን ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሌላውን ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።”
ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፤ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ ከእምነት ፈቀቅ በማለት መንገዳቸውን ስተው ሄደዋል፥ በብዙም ሥቃይ ራሳቸውን ወግተዋል።