መክብብ 3:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 የሰው ልጆችና የእንስሳ እድል ፈንታ አንድ ነው፥ አንድ ዓይነት መጨረሻ ይገጥማቸዋል፤ አንዱ እንደሚሞት ሌላውም እንዲሁ ይሞታል፥ የሁሉም እስትንፋስ አንድ ነው፥ ሁሉም ከንቱ ነውና ሰው ከእንስሳ ብልጫ የለውም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 የሰው ዕድል ፈንታ እንደ እንስሳት ነው፤ ሁለቱም ዕጣ ፈንታቸው አንድ ነው፤ አንዱ እንደሚሞት፣ ሌላውም እንዲሁ ይሞታል። ሁሉ አንድ ዐይነት እስትንፋስ አላቸው፤ ሰውም ከእንስሳ ብልጫ የለውም፤ ሁሉም ከንቱ ነው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 በእርግጥም የሰው ልጆችና የእንስሶች ዕድል ፈንታቸው አንድ ዐይነት ነው፤ አንዱ እንደሚሞት ሌላውም እንዲሁ ይሞታል፤ የሁለቱም የተፈጥሮ እስትንፋስ አንድ ዐይነት ነው፤ ታዲያ ሁለቱም ከንቱ ስለ ሆኑ ሰው ከእንስሳ አይሻልም። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ለሰው ልጆች ሞት አለባቸው፥ ለእንስሳም ሞት አለባቸው፤ አንድ ሞት አለባቸው፤ አንዱ እንደሚሞት ሌላውም እንዲሁ ይሞታል፤ ለሁሉም አንድ እስትንፋስ አላቸው፥ ሰው ከእንስሳ ብልጫው ምንድን ነው? ሁሉም ከንቱ ነውና ምንም የለውም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 የሰው ልጆችና የእንስሳ እድል ፈንታ አንድ ነው፥ ድርሻቸውም ትክክል ነው፥ አንዱ እንደሚሞት ሌላውም እንዲሁ ይሞታል፥ የሁሉም እስትንፋስ አንድ ነው፥ ሁሉም ከንቱ ነውና ሰው ከእንስሳ ብልጫ የለውም። Ver Capítulo |