መክብብ 3:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመውደድ ጊዜ አለው፥ ለመጥላትም ጊዜ አለው፥ ለጦርነት ጊዜ አለው፥ ለሰላምም ጊዜ አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመውደድ ጊዜ አለው፤ ለመጥላትም ጊዜ አለው፤ ለጦርነት ጊዜ አለው፤ ለሰላምም ጊዜ አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለመውደድ ጊዜ አለው፤ ለመጥላትም ጊዜ አለው፤ ለጦርነት ጊዜ አለው፤ ለሰላምም ጊዜ አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለመውደድ ጊዜ አለው፥ ለመጥላትም ጊዜ አለው፤ ለጦርነት ጊዜ አለው፥ ለሰላምም ጊዜ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለመውደድ ጊዜ አለው፥ ለመጥላትም ጊዜ አለው፥ ለጦርነት ጊዜ አለው፥ ለሰላምም ጊዜ አለው። |
ኢዮራምም “ኢዩ ሆይ፥ አመጣጥህ በሰላም ነውን?” ሲል ጠየቀ። ኢዩም፦ “እናትህ ኤልዛቤል ባመጣችው አስማትና የጣዖት አምልኮ ውስጥ ተነክረን እስካለን ድረስ ምን ሰላም አለ?” ሲል መለሰለት።
ባለ ራእዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፥ ንጉሡንም ኢዮሣፍጥን እንዲህ አለው፦ “ከሐዲውን ታግዛለህን? ወይስ ጌታን የሚጠሉትን ትወድዳለህን? ስለዚህም ነገር ከጌታ ዘንድ ቁጣ ሆኖብሃል።
በአንቺ በኩል አለፍሁ፥ አየሁሽም፥ እነሆ ጊዜሽ የፍቅር ጊዜ ነበር፥ እኔም መጐናጸፊያዬን በላይሽ ላይ ዘረጋሁና ዕርቃንሽን ሸፈንሁ፥ ማልሁልሽም ከአንቺም ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ አንቺም የእኔ ሆንሽ።
“ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት እንኳን ሳይቀር ካልናቀ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
ጌታም ለሙሴ እንደ ተናገረው ሁሉ ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ ያዘ፤ ኢያሱም ለእስራኤል እንደየነገዳቸው ድርሻ ርስት አድርጎ ምድሪቱን ሰጣቸው፤ ምድሪቱም ከጦርነት ዐረፈች።
“ሥራህንና ድካምህን ትዕግሥትህንም አውቃለሁ፤ ክፉዎችንም ልትታገሥ እንደማትችል፥ እንዲሁም ሐዋርያት ሳይሆኑ ‘ነን’ የሚሉትን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው አውቃለሁ፤