ያዕቆብም ለፈርዖን አለው፦ “የእንግድነቴ ዘመን መቶ ሠላሳ ዓመት ነው፥ የሕይወቴ ዘመኖች ጥቂትም ክፋም ሆኑብኝ፥ አባቶቼ በእንግድነት የተቀመጡበትንም ዘመን አያህሉም።”
መክብብ 2:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልቤ በጥበብ እየመራኝ፥ ሰውነቴን በወይን ጠጅ ደስ ለማሰኘት አላዋቂነትንም ለመያዝ በልቤ መረመርሁ፤ ይህም የሰው ልጆች በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ ከፀሐይ በታች ሊሠሩት የሚገባ መልካም ነገር ምን እንደሆነ እስካይ ድረስ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም አእምሮዬ በጥበብ እየመራኝ ራሴን በወይን ጠጅ ደስ ለማሠኘት፣ ሞኝነትንም ለመያዝ ሞከርሁ፤ ሰዎች በዐጭር የሕይወት ዘመናቸው ከሰማይ በታች ባለው ላይ ቢሠሩት ሊጠቅማቸው የሚችል ምን እንደ ሆነ ለማየት ፈለግሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ሁሉ ሆኖ ጥበብን ለማግኘት ባለኝ ምኞት በመመራት ልቤን በወይን ጠጅ እያስደሰትኩ የምዝናናበት ጊዜ እንዲኖረኝ ለማድረግ በሞኝነት ወሰንኩ፤ ሰዎች ሁሉ በምድር ላይ በሚኖሩበት በአጭር ዕድሜአቸው ሊያገኙት የሚገባ የተሻለ መልካም ዕድል ይህ ብቻ መሆኑን አሰብኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰው ልጆች በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ ከፀሐይ በታች የሚሠሩት መልካም ነገር ምን እንደ ሆነ እስካይ ድረስ ልቤ በጥበብ እየመራኝ፥ ሰውነቴን በወይን ደስ ለማሰኘት፥ ስንፍናንም ለመያዝ በልቤ መረመርሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰው ልጆች በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ ከፀሐይ በታች ሊሠሩት መልካም ነገር ምን እንደ ሆነ እስካይ ድረስ ልቤ በጥበብ እየመራኝ፥ ሰውነቴን በወይን ጠጅ ደስ ለማሰኘት ስንፍናንም ለመያዝ በልቤ መረመርሁ። |
ያዕቆብም ለፈርዖን አለው፦ “የእንግድነቴ ዘመን መቶ ሠላሳ ዓመት ነው፥ የሕይወቴ ዘመኖች ጥቂትም ክፋም ሆኑብኝ፥ አባቶቼ በእንግድነት የተቀመጡበትንም ዘመን አያህሉም።”
እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ ሀብትና ንብረት መስጠቱ፥ ከእርሷም ይበላና እድል ፈንታውን ይወስድ ዘንድ በድካሙም ደስ ይለው ዘንድ ሥልጣን መስጠቱ ነው፥ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው።
ሰው በከንቱ የሕይወቱ ቀናት ቍጥር ና እንደ ጥላ በሚያሳልፈው ዘመኑ በሕይወቱ ሳለ ለሰው የሚሻለውን የሚያውቅ ማነው? ወይስ ከፀሐይ በታች ከእርሱ በኋላ የሚሆነውን ለሰው ማን ይነግረዋል?
አውቅና እመረምር ዘንድ፥ ጥበብንና የነገሩን ሁሉ ትርጒም እፈልግ ዘንድ፥ ክፋትም አላዋቂነት፥ አላዋቂነትም እብደት እንደሆነ አውቅ ዘንድ እኔ በልቤ ዞርሁ።
ከመብላትና ከመጠጣት፥ ደስም ከመሰኘት በቀር ለሰው ልጅ ከፀሐይ በታች ሌላ ምንም መልካም ነገር የለውምና እኔ ደስታን አመሰገንሁ፥ ይህም እግዚአብሔር ከፀሐይም በታች በሰጠው በሕይወቱ ዘመን በድካሙ ከእርሱ ጋር ይኖራል።
“ሁለት ጌቶችን ማገልገል የሚችል ማንም የለም፤ አንዱን ጠልቶ ሌላውን ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሌላውን ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።”
አቢጌልም ወደ ናባል በተመለሰች ጊዜ፥ እነሆ፤ በቤቱ እንደ ንጉሥ ግብዣ ትልቅ ግብዣ አድርጎ አገኘችው፤ ክፉኛም ሰክሮ ልቡ በደስታ ተሞልቶ ነበር። ስለዚህ እስኪ ነጋ ድረስ ምንም አልነገረችውም።