መክብብ 11:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብርሃን ጣፋጭ ነው ፀሐይንም ማየት ለዐይን መልካም ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብርሃን መልካም ነው፤ ፀሓይንም ማየት ለዐይን ደስ ያሰኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብርሃን ታይቶ አይጠገብም፤ ስለዚህ የቀንን ብርሃን እያዩ መደሰት መልካም ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብርሃን ጣፋጭ ነው፥ ፀሓይንም ማየት ለዐይን መልካም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብርሃን ጣፋጭ ነው ፀሐይንም ማየት ለዓይን መልካም ነው። |
ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች፥ በክፉዎች ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት ደጃፍ ላይ መቅረትን መረጥሁ።
ይህን በማድረግ በሰማያት ላለው አባታችሁ ልጆች እንድትሆኑ ነው፤ እርሱ ለክፉዎችና ለደጎች ፀሐዩን ያወጣልና፥ ለጻድቃንና ለኃጥኣንም ዝናቡን ያዘንባልና።