መክብብ 1:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፀሐይ በታች የተሠራውን ሥራ ሁሉ አየሁ፥ እነሆም፥ ሁሉ ከንቱ ነው፥ ነፋስንም መከተል ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከፀሓይ በታች የተደረገውን ነገር ሁሉ አየሁ፤ ሁሉም ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ በዚህ ዓለም ላይ የተደረገውን ነገር ሁሉ ተመለከትኩ፤ ይሁን እንጂ ሁሉ ነገር ከንቱ ሆኖ አገኘሁት፤ ሁሉም ነገር ነፋስን እንደ መጨበጥ ሆኖ ይቈጠራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፀሐይ በታች የተሠራውን ሥራ ሁሉ አየሁ፤ እነሆም፥ ሁሉ ከንቱ ነው፥ ነፋስንም እንደ መከተል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፀሐይ በታች የተሠራውን ሥራ ሁሉ አየሁ፥ እነሆም፥ ሁሉ ከንቱ ነው፥ ነፋስንም እንደ መከተል ነው። |
እጄ የሠራቻትን ሥራዬን ሁሉ የደከምሁበትንም ድካሜን ሁሉ ተመለከትሁ፥ እነሆ፥ ሁሉ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነበረ፥ ከፀሐይ በታችም ትርፍ አልነበረም።
እርሱም ደስ ለሚያሰኘው ሰው ጥበብንና እውቀትን ደስታንም ይሰጠዋል፥ ለኃጢአተኛው ግን እግዚአብሔርን ደስ ለሚያሰኘው ሰው ይሰጥ ዘንድ እንዲሰበስብና እንዲያከማች ሥራን ይሰጠዋል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
የሰው ልጆችና የእንስሳ እድል ፈንታ አንድ ነው፥ አንድ ዓይነት መጨረሻ ይገጥማቸዋል፤ አንዱ እንደሚሞት ሌላውም እንዲሁ ይሞታል፥ የሁሉም እስትንፋስ አንድ ነው፥ ሁሉም ከንቱ ነውና ሰው ከእንስሳ ብልጫ የለውም።
ከእርሱ በፊት የተገዙለት ሕዝብ ሁሉ ስፍር ቍጥር አልነበራቸውም፥ በኋላ የሚመጡት ግን በእርሱ ደስ አይላቸውም። ይህም ደግሞ ከንቱ፥ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
ደግሞም የሰውን ድካምና የብልሃት ሥራውን ሁሉ ተመለከትሁ፥ በባልንጀራም ዘንድ ቅንዓት እንደሚያስነሣ አየሁ፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።