ዘዳግም 9:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እንደገና በታቤራ፥ በማሳህም፥ በቂብሮት ሐታዋም ጌታን አስቆጣችሁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተቤራም፣ በማሳህና በቂብሮት ሃታአባ እግዚአብሔርን አስቈጣችሁት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እንደገናም በታብዔራ፥ በማሳህና በቂብሮት ሐታዋ እግዚአብሔርን አስቈጣችሁት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በውዕየት፥ በፈተናም በምኞት መቃብርም እግዚአብሔርን አስቈጣችሁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በተቤራም በማሳህም በምኞት መቃብርም እግዚአብሔርን አስቆጣችሁት። |
እርሱም የዚያን ስፍራ ስም ማሳህና መሪባ ብሎ ጠራው፥ ይህም ስለ እስራኤል ልጆች ጥልና “ጌታ በመካከላችን ነው ወይስ አይደለም?” በማለት ጌታን ስለተፈታተኑት ነው።
ሙሴም አሮንን እንዲህ አለው፦ “ጥናህን ውሰድ፥ ከመሠዊያውም ላይ እሳት አድርግበት፥ ዕጣንም ጨምርበት፥ ወደ ማኅበሩም ፈጥነህ ውሰደው አስተስርይላቸውም፤ ከጌታ ዘንድ ቁጣ ወጥቶአልና መቅሠፍት ጀምሮአል።”
ስለ ሌዊም እንዲህ አለ፦ “ማሳህ በተባለው ቦታ ለፈተንኸው፥ በመሪባ ውኃም ለተከራከርኸው፥ ቱሚምህን ለሌዊ ስጠው፥ ኡሪምህም ለዚህ ቅዱስ ሰው ነው፤