ዘዳግም 8:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱን በመፍራትና የእርሱንም መንገድ በመከተል፥ የጌታ የአምላክህን ትእዛዞች ጠብቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመንገዶቹ በመሄድና እርሱንም በማክበር፣ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ጠብቅ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱን በመፍራትና የእርሱንም መንገድ በመከተል፥ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ሁሉ ጠብቅ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመንገዱም እንድትሄድ፥ እርሱንም እንድትፈራ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጠብቅ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመንገዱም እንድትሄድ እርሱንም እንድትፈራ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጠብቅ። |
እኔንም ለመፍራት ሁልጊዜም ትእዛዜን ሁሉ ለመጠበቅ፥ እንዲህ ያለ ልብ ምነው ሁልግዜ በኖራቸው! ለእነርሱ ለልጆቻቸውም ለዘለዓለም መልካም በሆነላቸው ነበር!