ዘዳግም 6:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም፥ ጌታ እንደሰጠህ ተስፋ፥ ጠላቶችህን ሁሉ ከፊትህ በማሳድድ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በተናገረው መሠረትም ጠላቶችህን ሁሉ ከፊትህ ታስወጣለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም የምታደርገው ጌታ በሰጠህ ተስፋ መሠረት ጠላቶችህን ሁሉ በማባረር ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንደ ተናገረ ጠላቶችህን ሁሉ ከፊትህ ያሳድድልህ ዘንድ። |
ድንበርህንም ከቀይ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፥ ከምድረበዳ እስከ ወንዙ ድረስ አደርጋለሁ፤ በምድሪቱ የሚኖሩትን በእጅህ እጥላለሁና፥ ከፊትህ ታባርራቸዋለህ።
መልካም እንዲሆንልህ፥ ጌታም ለአባቶችህ ወደ ማለላቸው ወደ መልካሚቱ ምድር ገብተህ እርሷን እንድትወርስ በጌታ ፊት ትክክልና መልካሙን አድርግ።