ዘዳግም 6:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመካከልህ ያለው ጌታ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነውና፥ የአምላክህ የጌታ ቁጣው እንዳይነድብህ፥ ከምድርም ፊት እንዳያጠፋህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም በመካከልህ ያለው አምላክህ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ስለ ሆነ፣ በአንተም ላይ ቍጣው ስለሚነድድ፣ ከምድር ገጽ ያጠፋሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባዕዳን አማልክትን ብታመልኩ በመካከላችሁ የሚገኘውን የአምላካችሁን ቊጣ ታስነሣላችሁ፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ስለ ሆነ ከምድር ገጽ ጠራርጎ ያጠፋችኋል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመካከልህ ያለው አምላክህ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነውና የአምላክህ የእግዚአብሔር ቁጣ እንዳይነድድብህ፥ ከምድርም ፊት እንዳያጠፋህ ተጠንቀቅ። |
እነርሱ ግን የጌታ ቁጣ በሕዝቡ ላይ እስኪወርድባቸው ድረስ፥ ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ፥ በጌታ መልክተኞች ይሳለቁ፥ ቃላቱንም ያቃልሉ፥ በነቢያቱም ላይ ያፌዙ ነበር።
አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም፤ እኔ ጌታ አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፥
ግብፃውያን ‘በተራራ መካከል ሊገድላቸው፥ ከገጸ ምድር ሊያጠፋቸው ለክፋት ነው ያወጣቸው’ ለምን ይበሉ? ከቁጣህ መዓት ተመለስ፥ በሕዝብህ ጥፋት ላይ ራራ።
መጻተኛውንና ድሀ አደጉን መበለቲቱንም ባትጨቊኑ፥ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን ባታፈስሱ፥ ክፉም እንዳይሆንባችሁ እንግዶችን አማልክት ባትከተሉ፥
እነሆ፥ የጌታ የእግዚአብሔር ዐይኖች በኃጢአተኛ መንግሥት ላይ ናቸው፥ ከምድርም ፊት አጠፋዋለሁ፤ ነገር ግን የያዕቆብን ቤት ፈጽሜ አላጠፋም፥” ይላል ጌታ።
የጌታም ቁጣ በላያችሁ እንዳይነድ፤ እርሱም ዝናብ እንዳይከለክላችሁ፤ ምድሪቱም ፍሬ እንዳትሰጥ ሰማያትን ይዘጋል፤ እናንተም ጌታ ከሚሰጣችሁ ከመልካሚቱ ምድር ወዲያውኑ ትጠፋላችሁ።”
በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፥ እኔ ጌታ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነኝና አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም።
እናንተ ግን ተመልሳችሁ በመካከላችሁ ወደ ቀሩት ወደ እነዚህ አሕዛብ ብትጠጉ፥ ከእነርሱም ጋር ብትጋቡ፥ እናንተም ከእነርሱ እነርሱም ከእናንተ ጋር በጋብቻ ቢተሳሰሩ፥
ጌታ አምላካችሁ ያዘዛችሁን ቃል ኪዳን ስታፈርሱ፥ ሄዳችሁም ሌሎችን አማልክት ስታመልኩ፥ ስትሰግዱላቸውም፥ በዚያ ጊዜ የጌታ ቁጣ ይነድድባችኋል፥ ከሰጣችሁም ከመልካሚቱ ምድር ፈጥናችሁ ትጠፋላችሁ።”