ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፥” ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው።
ዘዳግም 4:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ በአምላካችሁ ፊት በኮሬብ በቆማችሁበት ቀን፥ ጌታ፦ ‘ሕዝቡን ወደ እኔ ሰብስብ፥ በምድርም በሕይወት በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ እኔን መፍራት እንዲማሩ፥ ልጆቻቸውንም እንዲያስተምሩ፥ ቃሌን አሰማቸዋለሁ’ ብሎ በተናገረኝ ጊዜ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በምድሪቱ በሚኖሩበት ጊዜ ሁሉ እኔን ማክበር እንዲማሩ፣ ለልጆቻቸውም እንዲያስተምሩ ቃሌን ይሰሙ ዘንድ ሕዝቡን በፊቴ ሰብስብ” ባለኝ ጊዜ፣ በኮሬብ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት የቆማችሁበትን ዕለት አስታውሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ‘ቃሌን ይሰሙ ዘንድ ስለምፈልግ ሕዝቡን ሰብስብ’ ባለኝ ጊዜ በሲና ተራራ ላይ በእግዚአብሔር ፊት በቆማችሁበት ቀን ‘በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ ለእኔ እንዲታዘዙና፥ ልጆቻቸውም እኔን መፍራትን ያውቁ ዘንድ ያስተምሩአቸው’ ያለውን አስታውሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ሕዝቡን ወደ እኔ ሰብስባቸው፤ እነርሱ በምድር ላይ በሕይወት በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ እኔን መፍራት ይማሩና ለልጆቻቸውም ያስተምሩ ዘንድ ቃሌን ይስሙ ብሎኛልና በኮሬብ በተሰበሰባችሁ ጊዜ በፈጣሪያችሁ በእግዚአብሔር ፊት እንደ ቆማችሁ ንገራቸው። |
ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፥” ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው።
እንዲህም ሆነ በሦስተኛው ቀን ማለዳ ነጎድጓድ፥ መብረቅና ከባድ ደመና እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምጽ በተራራው ላይ ሆነ፤ በሰፈሩ የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተንቀጠቀጡ።
ጌታም ሙሴን፦ “ከአንተ ጋር ስነጋገር ሕዝቡ እንዲሰሙና ለዘለዓለም እንዲያምኑህ፥ እነሆ በከባድ ደመና እመጣለሁ” አለው። ሙሴም የሕዝቡን ቃል ለጌታ ነገረ።
“የአባቶቻችሁ አምላክ ጌታ፥ እንድትወርሷት በሰጣችሁ ምድር ላይ በምትኖሩበት ጊዜ ሁሉ፥ በጥንቃቄ ልትከተሏቸው የሚገባችሁ ሥርዓቶችና ሕጎች እነዚህ ናቸው።
ምንጊዜም ጌታ እግዚአብሔርን ማክበር ትማር ዘንድ፥ የወይን ጠጅና የዘይትህን አሥራት፥ የቀንድ ከብትህን፥ የበግና የፍየል መንጋህን በኵራት ስሙ እንዲጠራበት በሚመርጠው ስፍራ፥ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ትበላለህ።
አምላኩን ጌታን ማክበር ይማር ዘንድ፥ የዚህን ሕግ ቃል ሁሉና ይህን ሥርዓት በጥንቃቄ እንዲከተል ከእርሱ ጋር ይሁን፤ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ያንብበው፤
“ብቻ አስተውል፥ ነፍስህንም በትጋት ጠብቅ፤ ዐይኖችህ ያዩትን ነገር እንዳትረሳ፥ በሕይወትህም ዘመን ሁሉ ከልብህ እንዳይለይ፥ ለልጆችህም ለልጅ ልጆችህም አሳውቃቸው።
እኔንም ለመፍራት ሁልጊዜም ትእዛዜን ሁሉ ለመጠበቅ፥ እንዲህ ያለ ልብ ምነው ሁልግዜ በኖራቸው! ለእነርሱ ለልጆቻቸውም ለዘለዓለም መልካም በሆነላቸው ነበር!
አንተ ልጅህም የልጅ ልጅህም፥ በምትኖርበት ዘመን ሁሉ፤ ጌታ አምላክህን ፈርተህ እኔ ለአንተ ያዘዝሁትን፥ ሥርዓቱንና ትእዛዙን ሁሉ በመጠበቅ፥ ዕድሜህም ይረዝም ዘንድ፤
የሚናገረው እምቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነዚያ በምድር ላይ ሲያስረዳቸው እምቢ ያሉት ካላመለጡ፥ ከሰማይ የመጣው ሲያስጠነቅቀን ፈቀቅ የምንል እኛ እንዴት እናመልጣለን?