ዘዳግም 33:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ እንደ ጌታ ያለ ማንም የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንተን ለመርዳት በሰማያት ላይ፣ በደመናትም ላይ በግርማው እንደሚገሠግሥ፣ እንደ ይሹሩን አምላክ ያለ ማንም የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በሰማያዊ ግርማው አንተን ለመርዳት በሰማይና በደመና ላይ እንደ እኛ አምላክ እንደ እግዚአብሔር ማንም የለም የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ፍቁሩ አምላክ ማንም የለም፤ በሰማይ የሚኖረው፥ በጠፈርም በታላቅነት ያለው እርሱ ረዳትህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ 2 በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ 2 እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም። |
ከአማልክት መካከል ጌታ ሆይ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? በቅድስና ባለግርማ፥ በምስጋና የተፈራህ፥ ድንቅንም የምታደርግ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?
ስለ ግብጽ የተነገረ ትንቢት። እነሆ፥ ጌታ በፈጣን ደመና እየበረረ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጽም ጣዖታት በፊቱ ይርዳሉ፤ የግብጽም ልብ በውስጥዋ ይቀልጣል።
ከቶ እንዲህ ያለ ነገር ማን ሰምቶአል? እንዲህስ ያለ ነገር ማን አይቶአል? በውኑ አገር በአንድ ቀን ታምጣለችን? ወይስ በአንድ ጊዜ ሕዝብ ይወለዳል? ጽዮን እንዳማጠች ወዲያው ልጆችዋን ወልዳለችና።
ጌታ ሆይ ንዴትህ በወንዞች ላይ ነውን? ወይስ ቁጣህ በወንዞች ላይ ወይም መዓትህ በባሕር ላይ ነውን? በፈረሶችህ፥ በማዳን ሰረገሎች ላይ ተቀምጠሃልና።