በእንግድነት የምትኖርባትን ምድር፥ የከነዓን ምድር ሁሉ፥ ለዘለዓለም ግዛት ይሆንህ ዘንድ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ፥ አምላክም እሆናቸዋለሁ።”
ዘዳግም 32:49 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከኢያሪኮ ማዶ ባለው የሞዓብ ምድር፥ ከዓባሪም ተራራዎች አንዱ ወደ ሆነው ወደ ነቦ ተራራ ውጣ፥ ለእስራኤላውያን ርስት አድርጌ የምሰጣትን የከነዓንን ምድር አሻግረህ ተመልከት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከኢያሪኮ ማዶ ባለው የሞዓብ ምድር፣ ከዓባሪም ተራሮች አንዱ ወደ ሆነው ወደ ናባው ተራራ ወጥተህ ለእስራኤላውያን ርስት አድርጌ የምሰጣትን የከነዓንን ምድር አሻግረህ ተመልከት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በሞአብ ምድር በኢያሪኮ ከተማ ፊት ለፊት ወደሚገኙት የዐባሪም ተራራዎች ሂድ፤ ወደ ነቦ ተራራም ውጣ፤ ከዚያም ለእስራኤል ሕዝብ የማወርሳትን የከነዓንን ምድር አሻግረህ ተመልከት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በኢያሪኮ አንጻር በሞዓብ ምድር በዓባሪም ተራራ ውስጥ ወዳለው ወደ ናባው ተራራ ውጣ፤ ለእስራኤልም ልጆች ርስት አድርጌ የምሰጣቸውን የከነዓንን ምድር እያት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደዚህ በኢያሪኮ አንጻር በሞዓብ ምድር በዓባሪም ተራራ ውስጥ ወዳለው ወደ ናባው ተራራ ውጣ፥ ለእስራኤልም ልጆች ርስት አድርጌ የምሰጣቸውን የከነዓንን ምድር እይ፤ |
በእንግድነት የምትኖርባትን ምድር፥ የከነዓን ምድር ሁሉ፥ ለዘለዓለም ግዛት ይሆንህ ዘንድ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ፥ አምላክም እሆናቸዋለሁ።”
አባቶቻችንም ደግሞ በተራ ተቀብለው እግዚአብሔር በፊታቸው ያወጣቸውን የአሕዛብን አገር በያዙት ጊዜ ከኢያሱ ጋር አገቡአት፤ እስከ ዳዊት ዘመንም ድረስ ኖረች።
የምንኖርበት ምድራዊ ድንኳን የሆነው ሕይወት ቢፈርስ፥ በሰማይ ዘላለማዊ የሆነ በእጅ ያልተሠራ፥ በእግዚአብሔር የታነጸ መኖሪያ እንዳለን እናውቃለን።
ይህን ዮርዳኖስን አትሻገርምና ወደ ፒስጋ ራስ ውጣ፥ ዓይንህንም አንሥተህ ወደ ምዕራብና ሰሜንም ወደ ደቡብም ወደ ምሥራቅም በዓይንህ ተመልከት።