ዘዳግም 32:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈጽሜ እበትናቸዋለሁ፤ ከሰዎችም መካከል መታሰቢያቸውን አጠፋለሁ፤’ አልኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እበትናቸዋለሁ፤ ከሰዎችም መካከል መታሰቢያቸውን አጠፋለሁ አልሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ፈጽሜ እደመስሳቸዋለሁ፤ ከዚያም በኋላ የሚያስታውሳቸው አይኖርም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እበትናቸዋለሁ አልሁ፤ ከሰዎችም መካከል መታሰቢያቸውን አጠፋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እበትናቸዋለሁ አልሁ፤ 2 ከሰዎችም መካከል መታሰቢያቸውን አጠፋለሁ። |
ግብፃውያን ‘በተራራ መካከል ሊገድላቸው፥ ከገጸ ምድር ሊያጠፋቸው ለክፋት ነው ያወጣቸው’ ለምን ይበሉ? ከቁጣህ መዓት ተመለስ፥ በሕዝብህ ጥፋት ላይ ራራ።
“ጌታ በጠላቶችህ ፊት እንድትሸነፍ ያደርግሃል፤ በአንድ አቅጣጫ ትመጣባቸዋለህ፤ ነገር ግን በሰባት አቅጣጫ ከፊታቸው ትሸሻለህ፤ በሚደርስብህም ነገር ለምድር መንግሥታት ሁሉ ድንጋጤ ትሆናለህ።
“ከዚያም ጌታ ከአንዱ የምድር ዳርቻ እስከ ሌላው ዳርቻ በሕዝቦች ሁሉ መካከል ይበትንሃል። በዚያ አንተም ሆንህ አባቶችህ የማታውቋቸውን ከዕንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ ሌሎች አማልክትን ታመልካለህ።