ዘዳግም 31:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም የዚህን መዝሙር ቃል ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ፥ ለተሰበሰበው የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ በጆሮአቸው እንዲህ ሲል አሰማ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም የዚህን መዝሙር ቃል ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ፣ ለተሰበሰበው የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ በጆሯቸው እንዲህ ሲል አሰማ፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሙሴ በመላው የእስራኤል ጉባኤ ፊት የዚህን መዝሙር ቃሎች ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ አነበበ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም በእስራኤል ጉባኤ ሁሉ ጆሮ የዚህችን መዝሙር ቃሎች እስከ መጨረሻው ድረስ ተናገረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም በእስራኤል ጉባኤ ሁሉ ጆሮ የዚህች መዝሙር ቃሎች እስኪፈጸሙ ድረስ ተናገረ። |
እኔ ከሞትሁ በኋላ ፈጽማችሁ እንደምትረክሱ፥ ካዘዝኋችሁም መንገድ ዘወር እንደምትሉ ዐውቃለሁና። በጌታ ፊት ክፉ ድርጊት ስለምትፈጽሙ፥ እጆቻችሁ በሠሯቸውም ነገሮች እርሱን ስለምታስቆጡት በሚመጡት ዘመናት ጥፋት ይደርስባችኋል።”