ዘዳግም 3:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱንም ያንጊዜ አዘዝኩት፦ “ጌታ አምላካችሁ በእነዚህ በሁለቱ ነገሥታት ያደረገውን ሁሉ ዐይኖችህ አይተዋል፥ እንዲሁ ሁሉ በምታልፍባቸው መንግሥታት ላይ ጌታ ያደርጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ ኢያሱን እንዲህ ስል አዘዝሁት፤ “አምላካችሁ እግዚአብሔር በእነዚህ በሁለቱ ነገሥታት ላይ ያደረገውን ሁሉ በገዛ ዐይንህ አይተሃል፤ አሁንም ዐልፈህ በምትሄድባቸው መንግሥታት ላይ ሁሉ እግዚአብሔር ይህንኑ ይደግመዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከዚህም ቀጥሎ ኢያሱን እንዲህ ስል መከርኩት፤ ‘እግዚአብሔር አምላካችሁ ሲሖንና ዖግ ተብለው በሚጠሩት በሁለት ነገሥታት ያደረገውን በዐይናችሁ አይታችኋል፤ ምድሩን በምትወርሱበት በማንኛውም ሕዝብ ላይ ይህንኑ ተመሳሳይ ድርጊት ይደግመዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ጊዜ ኢያሱን እንዲህ ብዬ አዘዝሁት፦ አምላካችሁ እግዚአብሔር በእነዚህ በሁለቱ ነገሥት ያደረገውን ሁሉ ዐይኖችህ አይተዋል፤ እንዲሁ በምታልፍባቸው መንግሥታት ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ያደርጋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ጊዜ ኢያሱን፦ አምላካችሁ እግዚአብሔር በእነዚህ በሁለቱ ነገሥት ያደረገውን ሁሉ ዓይኖችህ አይተዋል፤ እንዲሁ በምታልፍባቸው መንግሥታት ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ያደርጋል። |
ይኸውም ጌታ እናንተን እንዳሳረፈ፥ ወንድሞቻችሁን እስኪያሳርፍ ድረስ እነርሱም ደግሞ በዮርዳኖስ ማዶ ጌታ አምላካችሁ የሚሰጣቸውን ምድር እስኪወርሱ ድረስ ነው፤ ከዚያም በኋላ እናንተ ሁሉ ወደ ሰጠኋችሁ ርስት ትመለሳላችሁ።”
ዓይንህ ያየችውን ታላቅን መቅሠፍት፥ ምልክትንም፥ ተአምራትንም፥ ጌታ አምላክህ ሲያስወጣህ የጸናችውን እጅ፥ የተዘረጋውንም ክንድ፥ እንደዚሁ ሁሉ ጌታ አምላክህ አንተ በምትፈራቸው በሕዝቦች ሁሉ ላይ ያደርጋል።