ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር በትውልዳቸው ለዘለዓለም ኪዳን አቆማለሁ፥ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ አምላክ እሆን ዘንድ።
ዘዳግም 29:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአንተ በሰጠው ተስፋና ለአባቶችህ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ በማለላቸው መሠረት እርሱ አምላክህ ይሆን ዘንድ፥ አንተም ሕዝቡ መሆንህን፥ በዛሬው ዕለት ለማረጋገጥ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለአንተ በሰጠው ተስፋና ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅና ለያዕቆብ በማለላቸው መሠረት እርሱ አምላክህ ይሆን ዘንድ፣ አንተም ሕዝቡ መሆንህን በዛሬው ዕለት ለማረጋገጥ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ይህን ያደረገው በሰጣችሁ ተስፋና ለአባቶቻችሁም ለአብርሃም፥ ለይስሐቅ፥ ለያዕቆብ በመሐላ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት እናንተን የራሱ ሕዝብ አድርጎ ሊመሠርታችሁ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዛሬ ለእርሱ ሕዝብ ያደርግህ ዘንድ፥ እርሱም ለአንተ እንደ ተናገረ ለአባቶችህም ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም እንደ ማለ አምላክ ይሆንልህ ዘንድ ነው። |
ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር በትውልዳቸው ለዘለዓለም ኪዳን አቆማለሁ፥ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ አምላክ እሆን ዘንድ።
በእንግድነት የምትኖርባትን ምድር፥ የከነዓን ምድር ሁሉ፥ ለዘለዓለም ግዛት ይሆንህ ዘንድ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ፥ አምላክም እሆናቸዋለሁ።”
አሁን ግን የሚበልጠውን ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ። ስለዚህ እግዚአብሔር ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና አምላካቸው ተብሎ ለመጠራት በእነርሱ አያፍርም።