ዘዳግም 27:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “‘የአባቱ ወይም የእናቱ ልጅ ከሆነችው እኅቱ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽም የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የአባቱ ወይም የእናቱ ልጅ ከሆነችው እኅቱ ጋራ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽም የተረገመ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ ‘ከእኅቱ ወይም በአንድ በኩል ብቻ እኅቱ ከሆነች ሴት ጋር ግንኙነት የሚፈጽም ወንድ ሁሉ የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይበሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከአባቱ ወይም ከእናቱ ልጅ ከእኅቱ ጋር የሚተኛ ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአባቱ ወይም ከእናቱ ልጅ ከእኅቱ ጋር የሚተኛ ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ። |
ሰውም ከጎረቤቱ ሚስት ጋር ርኩሰትን አደረገ፥ ሌላውም የልጁን ሚስት በዝሙት አረከሰ፥ ሌላውም በአንቺ ውስጥ የአባቱን ልጅ፥ እኅቱን አዋረደ።
የእኅትህን ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የአባትህ ልጅ ወይም የእናትህ ልጅ፥ በአገር ቤት ወይም በውጭ አገር የተወለደች ብትሆን፥ ኃፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ።
“ማናቸውም ሰው የአባቱን ልጅ ወይም የእናቱን ልጅ እኅቱን ቢያገባ፥ ኃፍረተ ሥጋዋንም ቢያይ፥ ኃፍረተ ሥጋውንም ብታይ፥ ይህ አሳፋሪ ነገር ነው፤ ከሕዝባቸውም ልጆች ፊት ተለይተው ይጥፉ፤ የእኅቱን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአልና በደሉን ይሸከማል።