ዘዳግም 26:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተም በጌታ እግዚአብሔር ፊት እንዲህ ብለህ ትናገራለህ፥ ‘አባቴ ከቦታ ወደ ቦታ በመዞር የሚኖር ሶርያዊ ነበር፤ ከጥቂት ሰዎችም ጋር ወደ ግብጽ ወርዶ እዚያ ተቀመጠ። ከዚያም ታላቅ፥ ኀያልና ቁጥሩ የበዛ ሕዝብ ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተም በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት እንዲህ ብለህ ትናገራለህ፤ “አባቴ ዘላን ሶርያዊ ነበር፤ ከጥቂት ሰዎችም ጋራ ወደ ግብጽ ወረደ፤ በዚያም ተቀመጠ፤ ታላቅ፣ ኀያልና ቍጥሩ የበዛ ሕዝብ ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያ በኋላ በእግዚአብሔር አምላክህ ፊት ይህን መግለጫ ስጥ፦ ‘አባቴ ከቦታ ወደ ቦታ በመዞር የሚኖር ሶርያዊ ነበር፤ ጥቂት ቤተሰብ ይዞ ወደ ግብጽ በመውረድ መጻተኛ ሆኖ ኖረ፤ ጥቂት የነበረው ታላቅ፥ ኀያል፥ ብዙ ሕዝብ ሆነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአምላክህም በእግዚአብሔር ፊት እንዲህ ብለህ ተናገር፦ አባቴ ከሶርያ ወጥቶ ወደ ግብፅ ወረደ፤ በዚያም በቍጥር ጥቂት ሆኖ ኖረ፤ በዚያም ታላቅና የበረታ፥ ብዙም ሕዝብ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአምላክህም በእግዚአብሔር ፊት እንዲህ ብለህ ተናገር፦ አባቴ የተቅበዘበዘ ሶርያዊ ነበረ፤ በቁጥር ጥቂት ሳለ ወደ ግብፅ ወረደ በዚያም ተቀመጠ፤ ታላቅ የሆነ የበረታም ቁጥሩም የበዛ ሕዝብ ሆነ። |
ዔሳውም አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት፥ ዔሳውም በልቡ አለ፦ “ለአባቴ የልቅሶ ቀን ቀርቦአል፥ ከዚያም በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።”
ይስሐቅም ያዕቆብን ላከው፥ እርሱም የያዕቆብና የዔሳው እናት የርብቃ ወንድም የሚሆን የሶርያዊ ባቱኤል ልጅ ላባ ወዳለበት ወደ ሁለቱ ወንዞች መካከል ሄደ።
በየስልቾቻችሁ አፍ ላይ የተገኘውን ብር መመለስ ስላለባችሁ፥ ዕጥፍ ገንዘብ ያዙ፤ ያ በየስልቾቻችሁ ውስጥ የተገኘው ብር ምናልባት በስሕተት የመጣ ሊሆን ይችላል።
ለዮሴፍ በግብጽ ከተወለዱት ከሁለቱ ወንዶች ልጆች ጋር፥ ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብጽ የገቡት የያዕቆብ ልጆችና የልጅ ልጆች ቊጥር በአጠቃላይ ሰባ ነበር።
“በምድር ልንቀመጥ በእንግድነት መጣን፥ ራብ በከነዓን ምድር እጅግ ጸንቶአልና፥ የአገልጋዮችህ በጎች የሚሰማሩበት ስፍራ የለም፥ አሁንም አገልጋዮችህ በጌሤም ምድር እንድንቀመጥ እንለምንሃለን።” አሉት ፈርዖንን።