ሌቦች ቢመጡብህ ወይም ወንበዴዎች በሌሊት ቢመጡ፥ የሚበቃቸውን ብቻ ይሰርቁ የለምን? ወይንንም የሚቆርጡ ወደ አንተ ቢመጡ ቃርሚያ ያስቀሩ የለምን? አንተ ግን ምንኛ ጠፋህ!
ዘዳግም 24:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወይን ተክልህን ፍሬ ስትሰበስብ ቃርሚያውን ለመሰብሰብ አትመለስበት፤ የቀረውን ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ተወው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የወይን ተክልህን ፍሬ ስትሰበስብ ቃርሚያውን ለመሰብሰብ አትመለስበት፤ የቀረውን ለመጻተኛው፣ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ተወው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወይንህንም ዘለላ በምትሰበስብበት ጊዜ የቀረውን ፍሬ ለመውሰድ ወደ ወይኑ ሐረግ ዳግመኛ አትመለስ፤ የቀሩትን ዘለላዎች ለመጻተኞች፥ ወላጆቻቸው ለሞቱባቸው ልጆችና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች ተውላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወይንህን ፍሬ በቈረጥህ ጊዜ ቃርሚያውን አትልቀመው፤ ለመጻተኛና ለድሃ-አደግ፥ ለመበለትም ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወይንህን ፍሬ በቈረጥህ ጊዜ ቃርሚያውን አትልቀመው፤ ለመጻተኛና ለድሀ አደግ ለመበለትም ይሁን። |
ሌቦች ቢመጡብህ ወይም ወንበዴዎች በሌሊት ቢመጡ፥ የሚበቃቸውን ብቻ ይሰርቁ የለምን? ወይንንም የሚቆርጡ ወደ አንተ ቢመጡ ቃርሚያ ያስቀሩ የለምን? አንተ ግን ምንኛ ጠፋህ!
“የዕርሻህን ሰብል በምታጭድበት ጊዜ፥ ተረስቶ የቀረ ነዶ ቢኖር፥ ያን ለመውሰድ ተመልሰህ አትሂድ። ጌታ እግዚአብሔር በእጅህ ሥራ ሁሉ እንዲባርክህ ነዶውን ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ተወው።
የወይራ ዛፍህን ፍሬ በምታራግፍበት ጊዜ በየቅርንጫፉላይ የቀረውን ለመቃረም ተመልሰህ አትሂድ፤ ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ተወው።