ዘዳግም 23:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእናንተ መካከል ሌሊት ዘር በማፍሰስ የረከሰ ሰው ቢኖር ከሰፈር ወደ ውጭ ይውጣ፥ እዚያው ይቆይ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከመካከላችሁ ሌሊት ዘር በማፍሰስ የረከሰ ሰው ቢኖር፣ ከሰፈር ወጥቶ እዚያው ይቈይ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ሰው ሌሊት በሕልሙ ከአባለ ዘሩ የፈሰሰ እርጥበት በሰውነቱ ላይ ቢገኝ ከሰፈር ወጥቶ በዚያው ይቈይ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእናንተ ውስጥ ሌሊት በሚሆነው ርኵሰት የረከሰ ሰው ቢኖር፥ ከሰፈር ወደ ውጭ ይውጣ፤ ወደ ሰፈርም አይግባ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእናንተ መካከል ሌሊት በሚሆነው ርኩሰት የረከስ ሰው ቢኖር፥ ከሰፈር ወደ ውጭ ይውጣ፥ ወደ ሰፈርም አይግባ። |
እናንተ ግን እርም ካደረጋችሁት በኋላ እርም ከሆነው ነገር ራሳችሁን ጠብቁ፤ እርም ከሆነው አንዳች የወሰዳችሁ እንደሆነ የእስራኤልን ሰፈር የተረገመ ታደርጉታላችሁ፥ ታስጨንቁታላችሁም።