ዘዳግም 22:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለቱን ወደዚያች ከተማ በር አውጡአቸው፥ ብላቴናይቱ በከተማ ውስጥ ሳለች አልጮኸችምና፥ ሰውዬውም የባልንጀራውን ሚስት አስነውሮአልና እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ውገሩአቸው፥ በዚህም ዓይነት ይህን ክፉ ነገር ከመካከላችሁ አስወግዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጃገረዲቱ በከተማ ውስጥ እያለች አስጥሉኝ ብላ ስላልጮኸች፣ ሰውየውም የሌላን ሰው ሚስት አስገድዶ ስለ ደፈረ፣ ሁለቱንም ወደ ከተማ ደጃፍ ወስዳችሁ እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ውገሯቸው። ክፉውን ከመካከልህ ማስወገድ አለብህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለቱንም ከከተማይቱ ወደ ውጪ አውጥታችሁ በድንጋይ ወግራችሁ ግደሉ፤ ልጃገረዲቱ መሞት የሚገባት ሰው ሊሰማ በሚችልበት ከተማ ውስጥ እያለች ርዳታ እንዲደረግላት የጩኸት ድምፅ ባለማሰማትዋ ነው፤ ሰውየውም የሚሞትበት ምክንያት ለሌላ ሰው ከታጨች ልጃገረድ ጋር በመተኛት ሕግን በማፍረሱ ነው፤ በዚህ ዐይነት ይህን ክፉ ነገር ከመካከላችሁ አስወግዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብላቴናዪቱ በከተማ ውስጥ ሳለች አልጮኸችምና፥ ሰውየውም የባልጀራውን ሚስት አስነውሮአልና በድንጋይ ወግረው ይግደሉአቸው፤ እንዲሁ ክፉውን ነገር ከውስጥህ ታስወግዳለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለቱን ወደዚያች ከተማ በር አውጡአቸው፤ ብላቴናይቱ በከተማ ውስጥ ሳለች አልጮኸችምና፥ ሰውዮውም የባልንጀራውን ሚስት አስነውሮአልና እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ውገሩአቸው፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ። |
እርሱ ይህን ሲያስብ ሳለ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፤ እንዲህም አለው “የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ! ከእርሷ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።
ከግብጽ ባወጣችሁና ከባርነት ምድር በዋጃችሁ በአምላካችሁ በጌታ ላይ ሊያስታችሁ ተናግሮአልና፥ አምላካችሁ ጌታ እንድትከተሉት ካዘዛችሁ መንገድ እንድትመለሱ አድርጎአልና፥ ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ይገደል፤ ስለዚህ ክፉውን ከመካከላችሁ አስወግዱ።”