ዘዳግም 21:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከጠላቶችህ ጋር ጦርነት ልትገጥም ወጥተህ አምላክህም ጌታ እነርሱን በእጅህ አሳልፎ ሰጥቶህ በማረክህ ጊዜ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጠላቶችህ ጋራ ጦርነት ልትገጥም ወጥተህ አምላክህ እግዚአብሔር እነርሱን በእጅህ አሳልፎ ሰጥቶህ በማረክህ ጊዜ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ጠላቶችህን ለመዋጋት ወጥተህ፥ እግዚአብሔር አምላክህ እነርሱን አሳልፎ ሲሰጥህና ስትማርካቸው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ጠላቶችህን ልትወጋ በወጣህ ጊዜ አምላክህም እግዚአብሔር በእጅህ አሳልፎ በሰጣቸውና በማረክሃቸው ጊዜ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጠላቶችህን ልትወጋ በወጣህ ጊዜ፥ አምላክህም እግዚአብሔር በእጅህ አሳልፎ በሰጣቸው በማረክሃቸውም ጊዜ፥ |
ጌታም ለአባቶቻቸው እንደ ማለላቸው በዙሪያቸው ካሉት አሳረፋቸው፤ ከጠላቶቻቸውም ሁሉ ማንም ሰው ሊቋቋማቸው አልቻለም፤ ጌታም ጠላቶቻቸውን ሁሉ በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው።