La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 19:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አለበለዚያ በተንኰል ሳይሆን ድንገት ሳያስበው ባልንጀራውን ቢገድል፥ መንገዱ ረጅም ከሆነ ደም ተበቃዩ በንዴት ተከታትሎ ይደርስበትና፥ መገደል የማይገባውን ሰው ሊገድል ይችላል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አለዚያ በተንኰል ሳይሆን ድንገት ሳያስበው ባልንጀራውን ቢገድል፣ መንገዱ ረዥም ከሆነ ደም ተበቃዩ በንዴት ተከታትሎ ይደርስበትና መገደል የማይገባውን ሰው ሊገድል ይችላል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ያለው የመጠለያ ከተማ፥ ርቀቱ ቶሎ የማይደረስበት ቢሆን ግን፥ ደሙን ለመበቀል መብት ያለው የሟቹ ዘመድ አባሮ ይዞ በደል የሌለበትን ያን ሰው በቊጣ ሊገድለው ይችላል፤ በእርግጥም ያ ሰው ጠላቱ ያልሆነውን ሰው የገደለው በአጋጣሚ ነበር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ባለ ደሙ ነፍሰ ገዳ​ዩን በልቡ ተና​ድዶ እን​ዳ​ያ​ሳ​ድ​ደው መን​ገ​ዱም ሩቅ ስለ​ሆነ አግ​ኝቶ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ለው፥ አስ​ቀ​ድሞ ጠላቱ አል​ነ​በ​ረ​ምና ሞት አይ​ገ​ባ​ውም።

Ver Capítulo



ዘዳግም 19:6
7 Referencias Cruzadas  

እነሆ ዘመዶቼ ሁሉ በአገልጋይህ ላይ ተነሥተው፥ ‘ወንድሙን የገደለውን ሰው አሳልፈሽ ስጪን፥ ወራሽ እንኳ ብናጠፋ ወንድሙን ስለ ገደለ እንገድለዋለን’ ይሉኛል፤ ስለዚህ የቀረኝን አንዱን መብራቴን በማጥፋት፥ ባሌን በምድር ላይ ያለ ስምና ያለ ዘር ሊያስቀሩት ነው።”


ነፍሰ ገዳዩ በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስኪቆም ድረስ እንዳይሞት፥ ከተሞቹ ከደም ተበቃይ የመማፀኛ ከተሞች ይሁኑላችሁ።


አንድ ሰው ከባልንጀራው ጋር እንጨት ሊቆርጥ ወደ ጫካ ቢሄድ፥ ዛፉን ለመጣል መጥረቢያውን በሚሰነዝርበት ጊዜ ብረቱ ከእጀታው ወልቆ ባልንጀራውን በመምታት ቢገድለው፥ ያ ሰው ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ በመሸሽ ሕይወቱን ማትረፍ ይችላል።


ሦስት ከተሞችን እንድትለይ ያዘዝሁህ በዚሁ ምክንያት ነው።


“አንደ ሰው ለሞት የሚያበቃ በደል ፈጽሞ ቢገደልና በድኑ በዕንጨት ላይ ቢሰቀል፤


ደም ተበቃዩ ቢያሳድደው፥ አስቀድሞ ሳይጠላው ባልንጀራውን ሳያውቅ ስለ ገደለው ነፍሰ ገዳዩን በእጁ አሳልፈው አይስጡት።