ዘዳግም 19:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቀሩትም ሰዎች ይህን ሰምተው ይፈራሉ፤ እንዲህ ያለው ክፉ ነገርም ለወደፊቱ በመካከልህ ከቶ አይደገምም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቀሩትም ሰዎች ይህን ሰምተው ይፈራሉ፤ እንዲህ ያለው ክፉ ነገርም ለወደፊቱ በመካከልህ ከቶ አይደገምም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎች ሁሉ ይህን ስለሚሰሙ ዳግመኛ እንደዚህ ያለ ክፉ ነገር በመካከልህ አያደርጉም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌላውም ሰምቶ ይፈራል፤ እንደዚህ ያለውንም ክፋት በመካከልህ ከእንግዲህ ወዲህ ደግሞ አያደርግም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀሩትም ሰምተው ይፈራሉ፥ እንደዚህ ያለውንም ክፋት ከመካከልህ ከእንግዲህ ወዲህ ደግሞ አያደርጉም። |
ከዚያም በኋላ የከተማዪቱ ሰዎች ሁሉ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩት፤ ክፉውንም ከመካከልህ አስወግድ፤ እስራኤልም ሁሉ ይህን ሰምቶ ይፈራል።