La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 18:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በጌታ ስም ቆሞ ለዘለዓለም ያገለግል ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር ከነገዶችህ ሁሉ እርሱንና ዘሮቹን መርጦአል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በእግዚአብሔር ስም ቆሞ ለዘላለም ያገለግል ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር ከነገዶችህ ሁሉ እርሱንና ዘሮቹን መርጧል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ለዘለዓለም በክህነት ያገለግሉ ዘንድ እግዚአብሔር ከነገዶቻችሁ መካከል የሌዊን ነገድ መርጦአል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እርሱ ከል​ጆቹ ጋር በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቁሞ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያገ​ለ​ግል ዘንድ፥ በስ​ሙም ይባ​ርክ ዘንድ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከነ​ገ​ዶ​ችህ ሁሉ መር​ጦ​ታ​ልና።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርሱ ከልጆቹ ጋር ተነሥቶ በእግዚአብሔር ስም ለዘላለም ያገለግል ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር ከነገዶችህ ሁሉ ስለ መረጠው ነው።

Ver Capítulo



ዘዳግም 18:5
9 Referencias Cruzadas  

አሮንንና ልጆቹን በመታጠቂያ ታስታጥቃቸዋለህ፥ ቆብን ታለብሳቸዋለህ፤ ክህነትም ለዘለዓለም ለእነርሱ የተወሰነ ይሆናል፥ እንዲሁም አሮንን እጅና የልጆቹን እጅ ትቀድሳለህ።


ለቆሬም እርሱንም ለተከሉት ሁሉ እንዲህ ቡሎ ተናገረ፦ “ነገ ጠዋት ጌታ ለእርሱ የሆነውን ሰው፥ ቅዱስም ማን እንሆነ፥ ወደ እርሱም ለመቅረብ የተፈቀደለትን ሰው ያሳውቃል፤ የመረጠውንም ሰው ወደ እርሱ እንዲቀርብ ይፈቅድለታል።


ለአምላኩም ቀንቶአልና፥ ለእስራኤልም ልጆች አስተስርዮአልና ለእርሱ ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ለዘለዓለም የክህነት ቃል ኪዳን ይሆንለታል።’ ”


አሮንንና ልጆቹን ሹማቸው፥ ክህነታቸውንም ይጠብቁ፤ ማናቸውም ሌላ ሰው ግን ቢቀርብ ይገደል።”


በዚያን ጊዜ የጌታን ቃል ኪዳን ታቦት እንዲሸከም፥ እርሱንም ለማገልገል በጌታ ፊት እንዲቆም፥ በስሙም እንዲባርክ ጌታ እስከ ዛሬ ድረስ የሌዊን ነገድ ለየ።


አምላክህን ጌታን ለማገልገል በዚያ የሚቆመውን ካህኑን ወይም ፈራጁን ባለመታዘዝ የሚዳፈር፥ ያ ሰው ይሙት፥ ከእስራኤልም መካከል ክፋትን አስወግድ፥