ዘዳግም 14:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰኰናው ስንጥቅ የሆነውን፥ ለሁለት የተከፈለውንና የሚያመሰኳውንም እንስሳ ሁሉ ትበላለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰኰናው ስንጥቅ የሆነውን፣ ለሁለት የተከፈለውንና የሚያመሰኳውን ማንኛውንም እንስሳ ብላ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአጠቃላይም ሰኮናቸው የተከፈለና የሚያመሰኩ እንስሶችን ትበላለህ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእንስሶች ሰኰናው የተሰነጠቀውን፥ ጥፍሩም ከሁለት የተከፈለውን፥ የሚያመሰኳውንም እንስሳ ሁሉ ትበላለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእንስሶች ሰኮናው የተሰነጠቀውን፥ ጥፍሩም ከሁለት የተከፈለውን፥ የሚያመሰኳውንም እንስሳ ሁሉ ትበላለህ። |
ነገር ግን ከሚያመሰኩት ወይም ሰኰናቸው ከተሰነጠቀ እንስሳት መካከል ግመልን፥ ጥንቸልንና ሽኮኮን አትብሉ፤ ምክንያቱም እነርሱ ቢያመሰኩሁም፥ ሰኰናቸው አልተሰነጠቀምና እነዚህ ለእናንተ ርኩሶች ናቸው።