ዘዳግም 1:45 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተመልሳችሁም በጌታ ፊት አለቀሳችሁ፥ እግዚአብሔር ግን ድምፃችሁን ሊሰማም፥ እናንተም ሊያዳምጥ አልወደደም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተም ተመልሳችሁ መጥታችሁ በእግዚአብሔር ፊት አለቀሳችሁ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ልቅሷችሁን አልሰማም፤ አላደመጣችሁምም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ይረዳችሁ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በመጮኽ አለቀሳችሁ፤ ነገር ግን ጩኸታችሁን ሊያዳምጥና ሊረዳችሁ አልወደደም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተቀምጣችሁም በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት አለቀሳችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ድምፃችሁን አልሰማም፤ ወደ እናንተም አልተመለከተም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተመልሳችሁም በእግዚአብሔር ፊት አለቀሳችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ድምፃችሁን አልሰማም፥ ወደ እናንተም አላዳመጠም። |