La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 1:43 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኔም ተናገርኋችሁ፥ እናንተ ግን በጌታ ትእዛዝ ላይ ዓመፃችሁ እንጂ አልሰማችሁም፥ በትዕቢታችሁም ወደ ተራራማው አገር ወጣችሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኔም ነገርኋችሁ፤ እናንተ ግን አላደመጣችሁም፤ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ዐምፃችሁ፣ በትዕቢታችሁ ወደ ተራራማው አገር ዘመታችሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ያለኝንም ለእናንተ ነገርኳችሁ፤ እናንተ ግን እምቢተኞች ሆናችሁ፤ በእርሱም ላይ ዐምፃችሁ በትዕቢታችሁ ብዛት ወደ ኮረብታማይቱ አገር ዘመታችሁ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኔም ተና​ገ​ር​ኋ​ችሁ፤ እና​ንተ ግን አል​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ተላ​ለ​ፋ​ችሁ፤ በኀ​ይ​ላ​ች​ሁም ወደ ተራ​ራ​ማው አገር ወጣ​ችሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኔም ተናገርኋችሁ፤ እናንተ ግን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ዓመፃችሁ እንጂ አልሰማችሁም፤ በትዕቢታችሁም ወደ ተራራማው አገር ወጣችሁ።

Ver Capítulo



ዘዳግም 1:43
8 Referencias Cruzadas  

እነርሱ ግን ዐመፁ ቅዱስ መንፈሱንም አስመረሩ፤ ስለዚህ ጠላታቸው ሆነ፤ እርሱ ራሱ ተዋጋቸው።


በማግስቱም ማልደው ተነሡ፥ ወደ ተራራውም ራስ እንዲህ እያሉ ወጡ፦ እነሆ፥ እኛ በዚህ አለን፤ እኛ ኃጢአትን ሠርተናልና ጌታ ወዳለው ስፍራ እንወጣለን።


የጌታ ቃል ኪዳን ታቦትና ሙሴ ከሰፈሩ ወጥተው ባይጓዙም እንኳ እነርሱ ግን ወደ ተራራው ራስ ለመውጣት ደፈሩ።


ነገር ግን የአገሩ ተወላጅ ቢሆን ወይም መጻተኛ ቢሆን፥ በትዕቢት ማናቸውንም ነገሮች የሚያደርግ ሰው ጌታን ሰድቦአል፤ ያም ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጠፋል።


“እናንተ አንገተ ደንዳኖች ልባችሁና ጆሮአችሁም ያልተገረዘ፤ እናንተ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ፤ አባቶቻችሁ እንደ ተቃወሙት እናንተ ደግሞ።


“እናንተ ግን በጌታ በአምላካችሁ ትእዛዝ ላይ ዓመፃችሁ እንጂ ወደ እርሷ መውጣትን አልፈቀዳችሁም፥


አምላክህን ጌታን ለማገልገል በዚያ የሚቆመውን ካህኑን ወይም ፈራጁን ባለመታዘዝ የሚዳፈር፥ ያ ሰው ይሙት፥ ከእስራኤልም መካከል ክፋትን አስወግድ፥