በዓሥራ አራተኛውም ዓመት ኮሎዶጎምርና ከእርሱ ጋር የነበሩት ነገሥታት መጡ፥ ራፋይምን በአስጣሮት ቃርናይም፥ ዙዚምንም በሃም፥ ኤሚምንም በሴዊ ቂርያታይም መቱ፥
ዘዳግም 1:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሐሴቦን ተቀምጦ የነበረውን የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን፥ በአስታሮትና በኤድራይ ተቀምጦ የነበረውን የባሳንን ንጉሥ ዐግን ከመታ በኋላ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ የሆነው በሐሴቦን ይገዛ የነበረውን የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንና በአስታሮት ይገዛ የነበረውን የዐግን ንጉሥ ባሳንን በኤድራይ ድል ካደረገ በኋላ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም የሆነው በሐሴቦን ከተማ ነግሦ ይገዛ የነበረውን የአሞራውያንን ንጉሥ ሲሖንንና በዐስታሮትና በኤድረዒ ከተሞች ሆኖ ይገዛ የነበረውን የባሳንን ንጉሥ ዖግን ድል ካደረገ በኋላ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሐሴቦን ተቀምጦ የነበረውን የአሞሬዎናውያንን ንጉሥ ሴዎንን፥ በአስጣሮትና በኤድራይን ተቀምጦ የነበረውንም የባሳንን ንጉሥ ዐግን ከገደሉት በኋላ፥ |
በዓሥራ አራተኛውም ዓመት ኮሎዶጎምርና ከእርሱ ጋር የነበሩት ነገሥታት መጡ፥ ራፋይምን በአስጣሮት ቃርናይም፥ ዙዚምንም በሃም፥ ኤሚምንም በሴዊ ቂርያታይም መቱ፥
እነርሱም የእርሱን ምድርና እንዲሁም በዮርዳኖስ ምሥራቅ የምትገኘውን ባሳንን ይገዛ የነበረውን የሌላውን አሞራዊ ንጉሥ የዖግን ምድር ወረሱ።