La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 1:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከምድሪቱም ፍሬ በእጃቸው ወሰዱ፥ ወደ እኛም ይዘውት መጡ፥ አሉንም፦ ‘ጌታ አምላካችን የሚሰጠን ምድር መልካም ናት።’

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከምድሪቱም ፍሬ ወደ እኛ ይዘው በመምጣት፣ “አምላካችን እግዚአብሔር የሚሰጠን ምድር መልካም ናት” ብለው ነገሩን።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚያም ካገኙት ፍሬ ጥቂቱን ይዘውልን መጡ፤ እግዚአብሔር አምላካችን ሊሰጠን ያቀዳት ምድር እጅግ ለም መሆንዋንም አስረዱን።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከም​ድ​ሪ​ቱም ፍሬ በእ​ጃ​ቸው ወሰዱ፤ ወደ እኛም ይዘ​ውት መጡ፦ ‘አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጠን ምድር መል​ካም ናት አሉን፤’

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከምድሪቱም ፍሬ በእጃቸው ወሰዱ፥ ወደ እኛም ይዘውት መጡ፦ አምላካችን እግዚአብሔር የሚሰጠን ምድር መልካም ናት ብለውም አወሩልን።

Ver Capítulo



ዘዳግም 1:25
6 Referencias Cruzadas  

ከግብፃውያን እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም አገር ወደ መልካምና ሰፊ አገር፥ ወተትና ማር ወደምታፈስሰው አገር ወደ ከነዓናውያን፥ ሒቲያውያን፥ ኤሞራውያን፥ ፌርዛውያን፥ ሒዊያውያን፥ የቡሳውያንም ስፍራ አወጣቸው ዘንድ ወረድሁ።


ምድሪቱም ለም ወይም መካን፥ ዛፍ ያለባት ወይም የሌለባት እንደ ሆነች ተመልከቱ፤ ከምድሪቱ ፍሬ አምጡ፤ አይዞአችሁ።” በዚያን ጊዜም ወይኑ አስቀድሞ ፍሬ የሚያፈራበት ወቅት ነበረ።


እንዲህም ብለው ነገሩት፦ “ወደ ላክኸን ምድር ገባን፥ እርሷም ወተትና ማር ታፈስሳለች፥ ፍሬዋም ይህ ነው።


ለእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲህ ብለው ተናገሩ፦ “ዞረን የሰለልናት ምድር እጅግ መልካም የሆነች ናት።


ሄዱም፥ ወደ ተራራማውም ወጡ፥ ወደ ኤሽኮልም ሸለቆ መጥተው ቃኙት።


“እናንተ ግን በጌታ በአምላካችሁ ትእዛዝ ላይ ዓመፃችሁ እንጂ ወደ እርሷ መውጣትን አልፈቀዳችሁም፥