ቈላስይስ 2:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጥምቀትም ከእርሱ ጋር ተቀብራችሁ፥ በጥምቀት ደግሞ ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር አሠራር በማመናችሁ ከእርሱ ጋር ተነሣችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጥምቀትም ከርሱ ጋራ ተቀብራችሁ፣ እርሱን ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር ኀይል በማመን ከርሱ ጋራ ደግሞ ተነሣችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተጠመቃችሁ ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ተቀበራችሁ፤ ከእርሱም ጋር ከሞት ተነሥታችኋል፤ ከሞት የተነሣችሁትም ክርስቶስን ከሞት ባስነሣው በእግዚአብሔር ኀይል በማመናችሁ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጥምቀትም ከእርሱ ጋር ተቀብራችኋል፤ በእርስዋም ከሙታን ለይቶ ባስነሣው በእግዚአብሔር ረዳትነትና በሃይማኖት ከእርሱ ጋር ተነሥታችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጥምቀትም ከእርሱ ጋር ተቀብራችሁ፥ በጥምቀት ደግሞ፥ ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር አሠራር በማመናችሁ፥ ከእርሱ ጋር ተነሣችሁ። |
በደረሱም ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑን ሰብስበው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ያደረገውን ሁሉ ለአሕዛብም የሃይማኖትን ደጅ እንደ ከፈተላቸው ተናገሩ።
ስለዚህ ወንድሞቼ ሆይ! እናንተ ደግሞ በክርስቶስ ሥጋ ለሕግ ተገድላችኋል፤ እናንተ ለሌላው፥ ከሙታን ለተነሣው፥ ለእርሱ እንድትሆኑና ለእግዚአብሔር ፍሬ እንድናፈራ ነው።
አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባርያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል።
እናንተም በበደላችሁና ሥጋችሁን ባለመገረዝ ሞታችሁ የነበራችሁትን በደላችንን ሁሉ ይቅር ባለን ጊዜ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ሕይወትን ሰጣችሁ፤
የእምነታችንንም ራስና ፍጽምና የሆነውን ኢየሱስን እንመልከት፤ እርሱ በፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉን ታግሦ፥ ውርደቱንም ንቆ፥ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአል።
ይህ ውሃ አሁን የጥምቀት ምሳሌ ሆኖ እናንተን ያድናል፤ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ ሳይሆን፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ፥ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የበጎ ሕሊና ልመና ነው።