ቈላስይስ 1:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንንም ከተወደደ ከእኛም ጋር አብሮ ባርያ ከሆነው ከኤጳፍራ ተማራችሁ፤ እርሱም ስለ እናንተ ታማኝ የክርስቶስ አገልጋይ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህንም ስለ እኛ የክርስቶስ ታማኝ አገልጋይ የሆነው፣ ዐብሮንም በአገልግሎት የተጠመደው ተወዳጁ ኤጳፍራ አስተማራችሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም በእኛ ምትክ የክርስቶስ ታማኝ አገልጋይ የሆነውና ከእኛም ጋር አብሮን የሚሠራው የተወደደው ኤጳፍራ ነግሮአችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ እናንተ የሚላክ በክርስቶስ የታመነ፥ የእኛም ወንድማችንና አገልጋያችን ከሚሆን ከኤጳፍራስ ተምራችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከተወደደ ከእኛም ጋር አብሮ ባሪያ ከሆነው ከኤጳፍራ እንዲህ ተማራችሁ፥ እርሱም ስለ እናንተ ታማኝ የክርስቶስ አገልጋይ ነው። |
በዚህ ምክንያት የተወደደውንና የታመነውን በጌታ ልጄ የሆነውን ጢሞቴዎስን ልኬላችኋለሁ፤ በየስፍራው በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እኔ እንደማስተምረው በክርስቶስ ኢየሱስ የሆነው መንገዴን እርሱ ያሳስባችኋል።
እንደ እብድ ሰው እናገራለሁ፤ እኔ እበልጣቸዋለሁ፤ በሥራ ብዙ ደክሜአለሁ፥ ብዙ ጊዜ ታስሬለሁ፥ ብዙ ግርፋት ደርሶብኛል፥ ብዙ ጊዜ እስከ መሞት ደርሻለሁ።
ነገር ግን ወንድሜንና ከእኔ ጋር አብሮ ሠራተኛና ወታደር፥ የእናንተ ግን መልእክተኛ የሆነውና የሚያስፈልገኝን የሚያገለግለውን ኤጳፍሮዲጡስን ወደ እናንተ መላክ ፍጹም አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፤
ከእናንተ ወገን የሆነ የክርስቶስ ባርያ ኤጳፍራ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ተረድታችሁና ፍጹማን ሆናችሁ እንድትቆሙ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ በጸሎቱ ይተጋል።
ቲቂቆስም ከእናንተ ወገን ከሆነውና ከታመነው ከተወደደውም ወንድም ከኦኔሲሞስ ጋር አብሮ ይመጣል። በእዚህም ሥፍራ ስላለው ሁኔታ ሁሉ ያስታውቋችኋል።
ይህን ትእዛዝ ለወንድሞች ብታሳውቅ፥ በእምነትና በተከተልኸው በመልካም ትምህርት ቃላት እየተመገብክ ያደግህ፥ የክርስቶስ ኢየሱስ መልካም አገልጋይ ትሆናለህ።
ስለዚህ የሕዝብን ኃጢአት ለማስተስረይ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን፥ በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው።