ፊልጵስዩስ 2:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 ነገር ግን ወንድሜንና ከእኔ ጋር አብሮ ሠራተኛና ወታደር፥ የእናንተ ግን መልእክተኛ የሆነውና የሚያስፈልገኝን የሚያገለግለውን ኤጳፍሮዲጡስን ወደ እናንተ መላክ ፍጹም አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፤ Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም25 እንዲሁም ወንድሜን፣ ዐብሮ ሠራተኛዬና ዐብሮኝ ወታደር የሆነውን፣ በሚያስፈልገኝ ሁሉ እንዲንከባከበኝ የላካችሁትን፣ የእናንተ መልእክተኛ የሆነውና አገልጋዩን አፍሮዲጡን መልሼ እንድልክላችሁ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 እንዲሁም እኔን በሚያስፈልገኝ ሁሉ እንዲረዳኝ ልካችሁት የነበረውን ወንድሜን ኤጳፍሮዲቱስን ወደ እናንተ መላክ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፤ እርሱ ከእኔ ጋር የተሰለፈ ወታደርና የሥራ ጓደኛዬ ሆኖ ሲሠራ የቈየ ነው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 አሁንም አብሮኝ የሚሠራውን ወንድማችንን አፍሮዲጡን ወደ እናንተ ልልከው አስቤአለሁ፤ እርሱም የክርስቶስ ሎሌ ነው፤ ለእናንተም መምህራችሁ ነው፤ ለእኔም ለችግሬ ጊዜ መልእክተኛዬ ነው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 ነገር ግን ወንድሜንና ከእኔ ጋር አብሮ ሠራተኛ ወታደርም የሚሆነውን፥ የእናንተ ግን መልእክተኛ የሆነውና የሚያስፈልገኝን የሚያገለግለውን አፍሮዲጡን እንድልክላችሁ በግድ አስባለሁ፤ Ver Capítulo |