አሞጽ 9:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ የሠራዊት አምላክ ምድርን ይዳስሳል እርሷም ትቀልጣለች፥ የሚኖሩባትም ሁሉ ያለቅሳሉ፤ ሞላዋም እንደ ግብጽ ወንዝ ትነሣለች፥ ዳግመኛም እንደ ግብጽ ወንዝ ትወርዳለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ እግዚአብሔር፣ የሰራዊት ጌታ፣ ምድርን ይዳስሳል፤ እርሷም ትቀልጣለች፤ በውስጧ የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ፤ የምድር ሁለመና እንደ አባይ ወንዝ ይነሣል፤ እንደ ግብጽ ወንዝም ይወርዳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መላዋ ምድር እንደ ግብጹ የዐባይ ወንዝ ከፍና ዝቅ በማለት ትናወጣለች፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድሪቱን ሲነካ ትቀልጣለች፤ በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉን የሚችል ጌታ እግዚአብሔር ምድርን ሁሉ ይዳስሳል፤ ያነዋውጣታልም፤ የሚኖሩባትም ሁሉ ያለቅሳሉ፤ ግድያ እንደ ወንዝ ይፈስሳል፤ ደግሞም እንደ ግብፅ ወንዝ ይወርዳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድርን ይዳስሳል እርስዋም ትቀልጣለች፥ የሚኖሩባትም ሁሉ ያለቅሳሉ፥ ሙላዋም እንደ ግብጽ ወንዝ ትነሣለች፥ ደግሞም እንደ ግብጽ ወንዝ ትወርዳለች። |
ምድሪቱ የምታለቅሰው፥ የአገሩ እጽዋት ሁሉ የሚደርቀው እስከ መቼ ነው? የተቀመጡባት ሰዎች፦ “ፍጻሜያችንን አያይም” ብለዋልና ስለ ክፋታቸው እንስሶችና ወፎች ተጠራርገው ጠፍተዋል።
በውኑ ምድሪቱ ስለዚህ ነገር አትናወጥምን? በእርሷም የሚኖር ሁሉ አያለቅስምን? ሞላዋም እንደ ግብጽ ወንዝ አትነሳምን? እንደ ግብጽም ወንዝ ተናውጣም ዳግመኛ አትወርድምን?”