La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




አሞጽ 7:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አሳየኝ፤ እነሆም፥ መከር ካለፈ በኋላ ያለው እህል በሚበቅልበት መጀመሪያ ላይ አንበጣን ፈጠረ፤ እነሆም፥ ከንጉሡ አጨዳ በኋላ ማንም ሰው ሳይዘራው የበቀለ ነበረ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጌታ እግዚአብሔር ይህን አሳየኝ፤ የንጉሡ የመኸር እህል ከተሰበሰበ በኋላ ገቦው መብቀል በጀመረ ጊዜ፣ እርሱ የአንበጣ መንጋ እንዲፈለፈል አደረገ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጌታ እግዚአብሔር ይህን ራእይ አሳየኝ፤ እነሆ የንጉሡ የመከር እህል ከታጨደ በኋላ እንደገና ገቦ ሆኖ በበቀለው እህል ላይ እግዚአብሔር የአንበጣ መንጋ እንዲፈለፈል አደረገ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ አሳ​የኝ፤ እነ​ሆም ከም​ሥ​ራቅ አን​በጣ ይመ​ጣል፤ አን​ዱም ኵብ​ኵባ ንጉሡ ጎግ ነበረ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አሳየኝ፥ እነሆም፥ የኋለኛው ሣር በሚበቅልበት መጀመሪያ ላይ አንበጣን ፈጠረ፥ እነሆም፥ ከንጉሡ አጨዳ በኋላ የበቀለ የገቦ ነበረ።

Ver Capítulo



አሞጽ 7:1
14 Referencias Cruzadas  

አንበጣ እንደሚሰበሰብ ምርኮአችሁ ትሰብስባለች፤ ኩብኩባም እንደሚዘል ሰዎች ይዘልሉበታል።


የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንን፥ የይሁዳንም አለቆች ጠራቢዎችንና ብረት ሠራተኞችን ከኢየሩሳሌም ማርኮ ወደ ባቢሎን ካፈለሳቸው በኋላ፥ ጌታ አሳየኝ፥ እነሆም፥ በጌታ መቅደስ ፊት ሁለት ቅርጫት በለስ ተቀምጠው ነበር።


ጌታ ያሳየኝን ነገር ሁሉ ለምርኮኞቹ ተናገርሁ።


ከተምች የቀረውን አንበጣ በላው፥ ከአንበጣም የቀረውን ደጎብያ በላው፥ ከደጎብያም የቀረውን ኩብኩባ በላው።


የሰደድሁባችሁ ታላቁ ሠራዊቴ አንበጣና ደጎብያ ኩብኩባና ተምች የበላቸውን ዓመታት እመልስላችኋለሁ።


“በዋግና በአረማሞ መታኋችሁ፤ የአታክልቶቻችሁንም ብዛት ወይኖቻችሁንም በለሶቻችሁንም ወይራዎቻችሁንም ተምች በላው፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥” ይላል ጌታ።


ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ አሳየኝ፤ እነሆም፥ ጌታ እግዚአብሔር በእሳት ለመፍረድ ጠራ፤ እርሷም ታላቁን ቀላይና ምድርን በላች።


እንዲህም አሳየኝ፤ እነሆም፥ ጌታ ቱንቢውን ይዞ በቱንቢ በተሠራ ቅጥር ላይ ቆሞ ነበር።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አሳየኝ፤ እነሆም፥ የበጋ ፍሬ የሞላበት ቅርጫት ነበረ።


ስለ እናንተ በላተኛውን እገሥጻለሁ፥ የአፈራችሁንም ፍሬ አያጠፋም፤ በእርሻችሁ ያለውንም ወይን ፍሬውን አያረግፍም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።