እርሱም ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱን፥ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የታላላቅ ሰዎችን ቤቶችና በከተማው ውስጥ የሚገኙትንም ሌሎች ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤
አሞጽ 2:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በይሁዳ ላይ እሳትን እልካለሁ፥ የኢየሩሳሌምንም የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኢየሩሳሌምን ምሽጎች እንዲበላ፣ በይሁዳ ላይ እሳት እሰድዳለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በይሁዳ ምድር ላይ እሳት እለቅበታለሁ፤ የኢየሩሳሌምንም ምሽጎች ያቃጥላል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በይሁዳ ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፤ የኢየሩሳሌምንም መሠረቶች ትበላለች።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በይሁዳ ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፥ የኢየሩሳሌምንም አዳራሾች ትበላለች። |
እርሱም ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱን፥ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የታላላቅ ሰዎችን ቤቶችና በከተማው ውስጥ የሚገኙትንም ሌሎች ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤
ነገር ግን የሰንበትን ቀን እንድትቀድሱ፥ በሰንበትም ቀን ሸክምን ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች እንዳትገቡ የነገርኋችሁን ባትሰሙኝ፥ በበሮችዋ ላይ እሳትን አነድዳለሁ፥ የኢየሩሳሌምንም የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች፥ አትጠፋምም።’ ”
ለመልካም ሳይሆን ለክፉ ፊቴን በዚህች ከተማ ላይ አድርጌአለሁና፤ ለባቢሎን ንጉሥ እጅ ትሰጣለች፥ እርሱም በእሳት ያቃጥላታል፥ ይላል ጌታ።’
እስራኤል ፈጣሪውን ረስቶአል፥ ቤተ መንግሥቶችን ሠርቶአል፤ ይሁዳም የተመሸጉትን ከተሞች አብዝቶአል፤ እኔ ግን በእርሱ ከተሞች ላይ እሳት እልካለሁ፥ የንጉሥ ቅጥሮቹንም ትበላለች።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ምድሪቱን በዙርያዋ ጠላት ይከባታል፤ ምሽግሽንም ከአንቺ ያፈርሳል፥ የንጉሥ ቅጥሮችሽም ይበዘበዛሉ።”