አሞጽ 2:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ ግን ናዝራውያኑን የወይን ጠጅ አጠጣችሁ፤ ነቢያቱንም፦ ትንቢትን አትናገሩ፥ ብላችሁ አዘዛችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እናንተ ግን ናዝራውያኑን የወይን ጠጅ አጠጣችኋቸው፤ ነቢያቱንም ትንቢት እንዳይናገሩ አዘዛችኋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ግን ናዝራውያንን የወይን ጠጅ በማጠጣት አሳታችሁ፤ ነቢያትንም ትንቢት እንዳይናገሩ ከለከላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እናንተ ግን ለእኔ የተለዩትን የወይን ጠጅ አጠጣችኋቸው፤ ነቢያቱንም፥ “ትንቢትን አትናገሩ ብላችሁ ከለከላችኋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ ግን ናዝራውያኑን የወይን ጠጅ አጠጣችኋቸው፥ ነቢያቱንም፦ ትንቢትን አትናገሩ ብላችሁ አዘዛችኋቸው። |
ከወይን ጠጅና ከሚያሰክር መጠጥ ራሱን ይለይ፤ ከወይን ወይም ከሚያሰክር መጠጥ የሚሠራን ሆምጣጤ አይጠጣ፥ ማንኛውንም ዓይነት የወይን ዘለላ ጭማቂ አይጠጣ፤ የወይን ዘለላ ወይም ዘቢብ አይብላ።