ሐዋርያት ሥራ 8:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንፈስም ፊልጶስን “ወደዚህ ሠረገላ ቅረብና ተገናኝ፤” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንፈስም ፊልጶስን፣ “ሂድ፤ ወደዚህ ሠረገላ ቅረብ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ፊልጶስን “ሂድ ወደዚያ ሠረገላ ቅረብና ተገናኘው” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንፈስ ቅዱስም ፊልጶስን፥ “ሂድ፤ ይህን ሰረገላ ተከተለው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንፈስም ፊልጶስን፦ “ወደዚህ ሰረገላ ቅረብና ተገናኝ” አለው። |
እኛም እንወቅ፤ ጌታን ለማወቅ እንትጋ፤ እንደ ንጋትም መገለጡ እርግጥ ነው፤ እንደ ዝናብ ምድርንም እንደሚያጠጣ እንደ በልግ ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።”
ወደ እኛም መጣና የጳውሎስን መታጠቂያ ወስዶ የገዛ እጁንና እግሩን አስሮ “እንዲሁ መንፈስ ቅዱስ ‘ይህ መታጠቂያ ያለውን ሰው አይሁድ በኢየሩሳሌም እንደዚህ ያስሩታል፤ በአሕዛብም እጅ አሳልፈው ይሰጡታል፤’ ይላል፤” አለ።
እርስ በርሳቸውም ባልተስማሙ ጊዜ፥ ጳውሎስ አንዲት ቃል ከተናገረ በኋላ ሄዱ፤ እንዲህም አለ፦ መንፈስ ቅዱስ በነቢዩ በኢሳይያስ ለአባቶቻችን
መንፈስ ግን በግልጥ እንዲህ ይላል በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና የአጋንንትን ትምህርት ትኩረት በመስጠት እምነትን ይክዳሉ፤