Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 8:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 መን​ፈስ ቅዱ​ስም ፊል​ጶ​ስን፥ “ሂድ፤ ይህን ሰረ​ገላ ተከ​ተ​ለው” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 መንፈስም ፊልጶስን፣ “ሂድ፤ ወደዚህ ሠረገላ ቅረብ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 መንፈስም ፊልጶስን “ወደዚህ ሠረገላ ቅረብና ተገናኝ፤” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 በዚህ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ፊልጶስን “ሂድ ወደዚያ ሠረገላ ቅረብና ተገናኘው” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 መንፈስም ፊልጶስን፦ “ወደዚህ ሰረገላ ቅረብና ተገናኝ” አለው።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 8:29
16 Referencias Cruzadas  

ጴጥ​ሮ​ስም ስለ ታየው ራእይ ሲያ​ወጣ ሲያ​ወ​ርድ መን​ፈስ ቅዱስ እን​ዲህ አለው፥ “እነሆ፥ ሦስት ሰዎች ይፈ​ል​ጉ​ሃል።


መን​ፈስ ቅዱ​ስም፦ ‘ሳት​ጠ​ራ​ጠር አብ​ረ​ሃ​ቸው ሂድ’ አለኝ፤ እነ​ዚህ ስድ​ስቱ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንም ተከ​ት​ለ​ውኝ መጡና ወደ​ዚያ ሰው ቤት ገባን።


መንፈስ ግን በግልጥ “በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ፤” ይላል፤ በገዛ ሕሊናቸው እንደሚቃጠሉ ደንዝዘው፥


ወደ እኛም መጣና የጳ​ው​ሎ​ስን መታ​ጠ​ቂያ አን​ሥቶ እጁ​ንና እግ​ሩን በገዛ እጁ አስሮ እን​ዲህ አለ፥ “መን​ፈስ ቅዱስ እን​ዲህ ይላል፤ የዚ​ህን መታ​ጠ​ቂያ ጌታ አይ​ሁድ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ዲህ ያስ​ሩ​ታል፤ ለአ​ሕ​ዛ​ብም አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​ታል።”


እን​ወ​ቀው፤ እና​ው​ቀ​ውም ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ከ​ተል፤ እንደ ወገ​ግ​ታም ተዘ​ጋ​ጅቶ እና​ገ​ኘ​ዋ​ለን፤ በም​ድ​ርም ላይ እንደ መጀ​መ​ሪ​ያ​ውና እንደ ኋለ​ኛው ዝናብ ወደ እኛ ይመ​ጣል።


“እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ሳይ​ጠሩ እመ​ል​ስ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ገናም ሲና​ገሩ እነሆ፥ አለሁ እላ​ቸ​ዋ​ለሁ።


በዚ​ህም ሁሉ ያው አንዱ መን​ፈስ ቅዱስ ሁሉን ይረ​ዳል፤ ለሁ​ሉም እንደ ወደደ ያድ​ላ​ቸ​ዋል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም ፊል​ጶ​ስን ተና​ገ​ረው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “በቀ​ትር ጊዜ ተነ​ሣና በደ​ቡብ በኩል ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ጋዛ በሚ​ያ​ወ​ር​ደው በም​ድረ በዳው መን​ገድ ሂድ።”


ሲመ​ለ​ስም በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ ተቀ​ምጦ የነ​ቢዩ የኢ​ሳ​ይ​ያ​ስን መጽ​ሐፍ ያነብ ነበር።


ፊል​ጶ​ስም ፈጥኖ ደርሶ የነ​ቢ​ዩን የኢ​ሳ​ይ​ያ​ስን መጽ​ሐፍ ሲያ​ነብ ሰማው፤ ፊል​ጶ​ስም፥ “በውኑ የም​ታ​ነ​በ​ውን ታው​ቀ​ዋ​ለ​ህን?” አለው።


ከው​ኃ​ዉም ከወጡ በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ፊል​ጶ​ስን ነጥቆ ወሰ​ደው፤ ጃን​ደ​ረ​ባ​ዉም ከዚያ ወዲያ አላ​የ​ውም፤ ደስ እያ​ለ​ውም መን​ገ​ዱን ሄደ።


እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ባል​ተ​ስ​ማሙ ጊዜ ጳው​ሎስ አን​ዲት ቃል ከተ​ና​ገረ በኋላ ከእ​ርሱ ተመ​ለሱ፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “መን​ፈስ ቅዱስ በነ​ቢዩ በኢ​ሳ​ይ​ያስ አን​ደ​በት ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን በእ​ው​ነት እን​ዲህ ብሎ መል​ካም ነገር ተና​ግ​ሮ​አል።


መን​ፈስ ቅዱስ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “ዛሬ ቃሉን ብት​ሰሙ ልባ​ች​ሁን አታ​ጽኑ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios