እነሆም፥ ነቢይ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ አክዓብ ቀርቦ፦ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘ይህን ብዙ ጭፍራ ሁሉ ታያለህን? እነሆ፥ ዛሬ በእጅህ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃለህ’ አለ።”
ሐዋርያት ሥራ 7:59 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስጢፋኖስም “ጌታ ኢየሱስ ሆይ! ነፍሴን ተቀበል፤” ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስጢፋኖስም እየወገሩት ሳለ፣ “ጌታ ኢየሱስ ሆይ፤ ነፍሴን ተቀበላት፤” ብሎ ጸለየ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በድንጋይ ሲወግሩት ሳሉ እስጢፋኖስ፥ “ጌታ ኢየሱስ ሆይ! ነፍሴን ተቀበል!” ብሎ ጸለየ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስጢፋኖስም፥ “ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ፥ ነፍሴን ተቀበል” እያለ ሲጸልይ ይወግሩት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስጢፋኖስም፦ “ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ነፍሴን ተቀበል” ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር። |
እነሆም፥ ነቢይ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ አክዓብ ቀርቦ፦ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘ይህን ብዙ ጭፍራ ሁሉ ታያለህን? እነሆ፥ ዛሬ በእጅህ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃለህ’ አለ።”
እንዲህም ይሆናል፥ የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፥ ጌታም እንደ ተናገረ፥ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም የሚተርፉ ይኖራሉ። ደግሞም ጌታ የጠራቸው ይገኛሉ።
የሰሙትም ሁሉ ተገረሙና “ይህ በኢየሩሳሌም ይህን ስም የሚጠሩትን ያጠፋ አይደለምን? ስለዚህስ ታስረው ወደ ካህናት አለቆች ይወስዳቸው ዘንድ ወደዚህ አልመጣምን?” አሉ።
በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱት፥ ቅዱሳን ለመሆን ለተጠሩት፥ የእነርሱና የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ከሚጠሩት ሁሉ ጋር፤