በሠላሳኛው ዓመት፥ በአራተኛው ወር፥ ከወሩም በአምስተኛው ቀን፥ በኮቦር ወንዝ በምርኮኞች መካከል ነበርሁ፥ ሰማያት ተከፈቱ፥ እኔም የእግዚአብሔርን ራእይ አየሁ።
ሐዋርያት ሥራ 7:56 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እነሆ፥ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ፤” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እነሆ፤ ሰማያት ተከፍተው፣ የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ “እነሆ፥ ሰማይ ተከፍቶ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እነሆ ሰማይ ተከፍቶ፤ የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “እነሆ፥ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ” አለ። |
በሠላሳኛው ዓመት፥ በአራተኛው ወር፥ ከወሩም በአምስተኛው ቀን፥ በኮቦር ወንዝ በምርኮኞች መካከል ነበርሁ፥ ሰማያት ተከፈቱ፥ እኔም የእግዚአብሔርን ራእይ አየሁ።
ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያውኑ ከውኃ ወጣ፤ እነሆ ሰማያት ተከፈቱ፤ የእግዚአብሔር መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድና በእርሱ ላይ ሲያርፍ አየ፤
በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተከፈተ፤ የኪዳኑም ታቦት በቤተ በመቅደሱ ታየ፤ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።
ከዚያ በኋላም አየሁ፤ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ! እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምፅ “ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ መሆን ያለበትን ነገር አሳይሃለሁ፤” አለ።