ሐዋርያት ሥራ 6:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሐዋርያትም ፊት አቆሙአቸው፤ ከጸለዩም በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህንም አምጥተው ሐዋርያት ፊት አቀረቧቸው፤ እነርሱም ከጸለዩ በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህን በሐዋርያት ፊት አቆሙአቸው፤ ሐዋርያትም ከጸለዩ በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሐዋርያትም ፊት አቆሙአቸው፤ ጸልየውም እጃቸውን በራሳቸው ላይ ጫኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሐዋርያትም ፊት አቆሙአቸው፥ ከጸለዩም በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው። |
ሲጸልዩም “የሁሉን ልብ የምታውቅ አንተ ጌታ ሆይ! ይሁዳ ወደ ገዛ ራሱ ስፍራ ይሄድ ዘንድ በተዋት በዚህች አገልግሎትና ሐዋርያነት ስፍራን እንዲቀበል የመረጥኸውን ከእነዚህ ከሁለቱ አንዱን ሹመው፤” አሉ።
ሐናንያም ሄዶ ወደ ቤቱ ገባ፤ እጁንም ጭኖበት “ወንድሜ ሳውል ሆይ! ጌታ፥ እርሱም በመጣህበት መንገድ የታየህ ኢየሱስ ነው፤ ደግሞ ታይ ዘንድና መንፈስ ቅዱስ ይሞላብህ ዘንድ ላከኝ፤” አለ።