ሐዋርያት ሥራ 5:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመቅደስ አዛዥና የካህናት አለቆችም ይህን ነገር በሰሙ ጊዜ “እንጃ ይህ ምን ይሆን?” እያሉ ስለ እነርሱ አመነቱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቤተ መቅደሱ ጥበቃ ሹምና የካህናት አለቆችም ይህን በሰሙ ጊዜ በነገሩ ተገረሙ፤ ግራም ተጋቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቤተ መቅደሱ የዘብ አዛዥና የካህናት አለቆች ይህን በሰሙ ጊዜ “ይህ ነገር ምን ይሆን?” በማለት ግራ ተጋቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሊቃነ ካህናትና የቤተ መቅደሱ ሹምም ይህን ነገር በሰሙ ጊዜ፥ የሚያደርጉትን አጥተው፥ “እንጃ ይህ ምን ይሆን?” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመቅደስ አዛዥና የካህናት አለቆችም ይህን ነገር በሰሙ ጊዜ፦ “እንጃ ይህ ምን ይሆን?” እያሉ ስለ እነርሱ አመነቱ። |
ኢየሱስም ወደ እርሱ ለመጡበት ለካህናት አለቆችና ለቤተ መቅደስ አዛዦች ለሽማግሌዎችም “ወንበዴን እንደምትይዙ ሰይፍና ዱላ ይዛችሁ መጣችሁን?
እነርሱም እንደምን እንደሚቀጡ ምክንያት ስላላገኙባቸው፥ እንደገና ዝተው ከሕዝቡ የተነሣ ፈቱአቸው፤ ሰዎች ሁሉ ስለ ሆነው ነገር እግዚአብሔርን ያከብሩ ነበርና።